ናሆም 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስፍራዋን ግን በሚያጥለቀልቅ ጎርፍ ፈጽሞ ያጠፋታል፥ ጠላቶቹንም ወደ ጨለማ ያሳድዳቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነነዌን ግን፣ በሚያጥለቀልቅ ጐርፍ ያጠፋታል፤ ጠላቶቹንም ወደ ጨለማ ያሳድዳቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስፍራዋን ግን በሚያጥለቀልቅ ጎርፍ ፈጽሞ ያጠፋታል፥ ጠላቶቹን ጨለማ ያሳድዳቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተቃዋሚዎቹን በኀይለኛ ጐርፍ ያጥለቀልቃቸዋል፤ ጠላቶቹንም ወደ ጨለማ ያሳድዳቸዋል። |
የሰማይም ከዋክብትና ኦሪዎን፥ የሰማይ ሠራዊትም ሁሉ ብርሃናቸውን አይሰጡም፤ ፀሐይም በወጣች ጊዜ ትጨልማለች፤ ጨረቃም በብርሃኑ አያበራም።
እነሆ፥ ምድሪቱን ባድማ ሊያደርግ፥ ኀጢአተኞችዋንም ከእርስዋ ዘንድ ሊያጠፋ በመዓትና በጽኑ ቍጣ ተሞልቶ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል።
ፍርዴን ለተስፋ ይቅርታዬንም ለትክክለኛ ሚዛን አደርጋለሁ፤ በከንቱና በሐሰት የሚታመኑ ከዐውሎ ነፋስ አያመልጡም።
ከሞትም ጋር ያደረጋችሁት ቃል ኪዳን ይፈርሳል፤ ከኢኦልም ጋር የተማማላችሁት መሐላ አይጸናም፤ የሚያልፍ ዐውሎ ነፋስ በመጣ ጊዜ ይረግጣችኋል፤ ትደክማላችሁም።
እነሆ፥ ኀያል ብርቱ የሆነ የእግዚአብሔር መቅሠፍት በኀይል እንደሚወርድ የበረዶ ወጨፎ፥ እንደሚያጠፋም ዐውሎ ነፋስ፥ እንደሚያጥለቀልቅም እንደ ብዙ ውኃ ፈሳሽ በጠነከረ እጅ ወደ ምድር ይጥላል።
ወደ ታችም ወደ ምድር ትመለከታላችሁ፤ ድቅድቅ ጨለማንም ታያላችሁ፤ ታላቅ መከራንም ትቀበላላችሁ፤ ትጨነቃላችሁ፤ ትቸገራላችሁም፤ በፊታችሁም ጨለማ ይሆናል፤ አታዩምም፤ በመከራም ያለ ጊዜው እስኪደርስ አይድንም።
ሳይጨልምባችሁ፥ ጨለማም ባለባቸው ተራሮች እግሮቻችሁ ሳይሰነካከሉ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ፤ በዚያም የሞት ጥላ አለና በጨለማውም ውስጥ ያኖራችኋልና ብርሃንን ተስፋ ታደርጋላችሁ።
አንተም፦ እኔ ከማመጣባት ክፉ ነገር የተነሣ እንዲሁ ባቢሎን ትሰጥማለች፤ አትነሣምም በል።” የኤርምያስ ቃል እስከዚህ ድረስ ነው።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመዓቴ በዐውሎ ነፋስ እሰነጣጥቀዋለሁ፤ ያጠፋውም ዘንድ በቍጣዬ የሚያሰጥም ዝናብ፥ በመዓቴም ታላቅ የበረዶ ድንጋይ አወርዳለሁ።
በውኑ ምድሪቱ ስለዚህ ነገር አትናወጥምን? በእርስዋም የሚኖር ሁሉ አያለቅስምን? ጦርነት እንደ ወንዝ ይፈስሳል፤ እንደ ግብፅም ወንዝ ይሞላል፤ ደግሞም ይወርዳል።