ማቴዎስ 6:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ብል ሊበላው፣ ዝገት ሊያበላሸው፣ ሌባም ቈፍሮ ሊሰርቀው በሚችልበት በዚህ ምድር ላይ ለራሳችሁ ሀብት አታከማቹ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ብልና ዝገት በሚያጠፉት፥ ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁበት በምድር ላይ ሃብት አትሰብስቡ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ብልና ዝገት በሚያጠፉበት፥ ሌቦችም ሰብረው በሚሰርቁበት፥ በዚህ ምድር ላይ ለራሳችሁ ሀብት አታከማቹ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤ |
መሥዋዕትንና ቍርባንን አልወደድሁም፤ ሥጋህን አንጻልኝ፤ የሚቃጠለውንና ስለ ኀጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልወደድሁም።
በቍጣ ቀን ገንዘብ አይጠቅምም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች። ጻድቅ በሞተ ጊዜ ጸጸትን ይተዋል፥ የኀጢአተኛ ሞት ግን በእጅ የተያዘና ሣቅ ይሆናል።
እርሱ በፊቱ ደግ ለሆነ ሰው ጥበብንና ዕውቀትን፥ ደስታንም ይሰጠዋል፤ ለኀጢአተኛ ግን በእግዚአብሔር ፊት ደግ ለሆነ ይሰጥ ዘንድ እንዲሰበስብና እንዲያከማች ጥረትን ይሰጠዋል። ይህ ደግሞ ከንቱ፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
በእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፣ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ፈጥኖ ይጨርሳቸዋልና ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች።
ሀብታችሁን ሸጣችሁ ምጽዋት ስጡ፤ ሌባ በማያገኝበት ነቀዝም በማያበላሽበት፥ የማያረጅ ከረጢት፥ የማያልቅም መዝገብ በሰማያት ለእናንተ አድርጉ።
ነገር ግን ይህን ዕወቁ፤ ባለቤት ሌባ የሚመጣበትን ጊዜ ቢያውቅ ተግቶ በጠበቀ፥ ቤቱንም እንዲቈፍሩት ባልፈቀደም ነበር።
ጌታችን ኢየሱስም ይህን ሰምቶ እንዲህ አለው፥ “አንዲት ቀርታሃለች፤ ሂድና ያለህን ሁሉ ሸጠህ ለነዳያን ስጥ፤ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ፤ መጥተህም ተከተለኝ።”
ጌታችን ኢየሱስም እጅግ ሲያዝን አይቶ እንዲህ አለ፥ “ገንዘብ ላላቸው ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው!
በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ፥ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።