Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 31:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 “ወር​ቄን በመ​ሬት ውስጥ ቀብሬ እንደ ሆነ፥ ዋጋው ብዙ በሆነ ዕንቍ ታም​ኜም እንደ ሆነ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 “ወርቅን ተስፋ አድርጌ፣ ወይም ንጹሑን ወርቅ፣ ‘አንተ መታመኛዬ ነህ’ ብዬ ከሆነ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 “ወርቅን ተስፋ አድርጌ፥ ንጹሑንም ወርቅም መተማመኛዬ ብዬ ጠርቼው እንደሆነ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 “እምነቴን በሀብት ላይ አድርጌ አላውቅም፤ ወይም ንጹሕ ወርቅንም መታመኛዬ አላደረግሁም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ወርቅን ተስፋ አድርጌ፥ ጥሩውንም ወርቅ፦ በአንተ እታመናለሁ ብዬ እንደ ሆነ፥

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 31:24
18 Referencias Cruzadas  

ያዕ​ቆ​ብም የላባ ልጆች ያሉ​ትን ነገር፥ “ያዕ​ቆብ ለአ​ባ​ታ​ችን የሆ​ነ​ውን ሁሉ ወሰደ፤ ይህ​ንም ሁሉ ክብር ከአ​ባ​ታ​ችን ከብት አገኘ” ሲሉ ሰማ።


በዓ​ለቱ ቋጥኝ ላይ ለራ​ስህ መዝ​ገ​ብን ታኖ​ራ​ለህ። የሶ​ፎ​ርም ወርቅ እንደ ጅረት ድን​ጋይ ይሆ​ን​ል​ሃል።


አን​ተስ ተግ​ሣ​ጼን ጠላህ፥ ቃሌ​ንም ወደ ኋላህ መለ​ስኽ።


በሰ​ይፍ እጅ አል​ፈው ይሰጡ፥ የቀ​በ​ሮ​ዎ​ችም ዕድል ፋንታ ይሁኑ።


የባለጠጋ ሀብት የጸናች ከተማ ናት፤ የዕውቀት ድህነት ግን የኀጢአተኞች ጥፋት ነው።


በባለጠግነቱ የሚተማመን ሰው ይወድቃል፤ ጻድቃንን የሚቀበል ግን ይለመልማል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ጠቢብ በጥ​በቡ አይ​መካ፤ ኀያ​ልም በኀ​ይሉ አይ​መካ፤ ባለ​ጠ​ጋም በብ​ል​ጥ​ግ​ናው አይ​መካ፤


በታ​ላቅ ጥበ​ብ​ህና በን​ግ​ድህ ብል​ጽ​ግ​ና​ህን አብ​ዝ​ተ​ሃል፤ በብ​ል​ጽ​ግ​ና​ህም ልብህ ኰር​ቶ​አል።


ኢየሱስም ዘወር ብሎ አይቶ ደቀ መዛሙርቱን “ገንዘብ ላላቸው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ይሆናል፤” አላቸው።


“ዕወቁ፤ ከቅ​ሚ​ያም ሁሉ ተጠ​በቁ፤ ሰው የሚ​ድን ገን​ዘብ በማ​ብ​ዛት አይ​ደ​ለ​ምና” አላ​ቸው።


ምድ​ራዊ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁ​ንም ከዝ​ሙ​ትና ከር​ኵ​ሰት፥ ከጥ​ፋ​ትና ከክፉ ምኞት፥ ጣዖት ማም​ለክ ከሆ​ነው ከቅ​ሚ​ያም ግደ​ሉት።


ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፤ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።


በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ፥ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios