ኢየሱስ ግን ዝም አለ። ሊቀ ካህናቱም “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደ ሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ፤” አለው።
ማቴዎስ 27:54 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመቶ አለቃም ከእርሱም ጋር ኢየሱስን የሚጠብቁ መናወጡንና የሆነውን ነገር አይተው “ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ፤” ብለው እጅግ ፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመቶ አለቃውና ዐብረውት ኢየሱስን ይጠብቁት የነበሩት የመሬት መናወጡንና የሆነውን ነገር ሁሉ ባዩ ጊዜ እጅግ ፈርተው፣ “ይህስ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበር!” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመቶ አለቃውና ከእርሱም ጋር ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩት የምድርን መናወጥና የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ እጅግ ፈርተው “በእውነት ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነበር” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመቶ አለቃውና ከእርሱም ጋር ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩት የምድርን መናወጥና የሆነውንም ነገር ባዩ ጊዜ እጅግ ፈርተው “በእውነት ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ!” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመቶ አለቃም ከእርሱም ጋር ኢየሱስን የሚጠብቁ መናወጡንና የሆነውን ነገር አይተው፦ ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ ብለው እጅግ ፈሩ። |
ኢየሱስ ግን ዝም አለ። ሊቀ ካህናቱም “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደ ሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ፤” አለው።
ሁሉም፥ “እንግዲያስ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህን?” አሉት፤ እርሱም፥ “እኔ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንሁ እናንተ ትላላችሁ” አላቸው።
አይሁድም መልሰው፥ “እኛ ሕግ አለን፤ እንደ ሕጋችንም ሊሞት ይገባል፤ ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ አድርጎአልና” አሉት።
ይህንም በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተከፈተ፤ ጴጥሮስንና ወንድሞቹ ሐዋርያትንም፥ “ወንድሞቻችን ሆይ፥ ምን እናድርግ?” አሏቸው።
በዚያ ጊዜም ጭፍሮቹን ከአለቆቻቸው ጋር ይዞ ወደ እነርሱ ሄደ፤ እነርሱም የሻለቃውን ጭፍሮች ባዩ ጊዜ ጳውሎስን መምታታቸውን ተዉ።
ከመቶ አለቆችም ሁለቱን ጠርቶ፥ “ከወታደሮች ሁለት መቶ ሰውና ሰባ ፈረሰኞች፥ ሁለት መቶ ቀስተኞችም ምረጡ፤ ከሌሊቱም በሦስት ሰዓት ወደ ቂሣርያ ይሂዱ” አላቸው።
ከዚህም በኋላ ፊስጦስ ወደ ቄሣር ወደ ኢጣልያ በመርከብ እንሄድ ዘንድ ባዘዘ ጊዜ ጳውሎስ ከሌሎች እስረኞች ጋር አብሮ የአውግስጦስ ጭፍራ ለነበረ ዩልዮስ ለሚባል የመቶ አለቃ ተሰጠ።
የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስን ሊያድነው ወድዶአልና ምክራቸውን እንቢ አለ፤ ዋና የሚያውቁትንም ዋኝተው ወደ ምድር እንዲወጡ አዘዛቸው።
የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በኀይሉና በመንፈስ ቅዱስ፥ ከሙታንም ተለይቶ በመነሣቱ ስለ አሳየ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፥
በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ከከተማይቱም ዐሥረኛው እጅ ወደቀ፤ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፤ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፤ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ።