ኢዩም ወደ ጌታው ብላቴኖች ወጣ፤ እነርሱም፥ “ደኅና ነውን? ይህ እብድ ለምን ወደ አንተ መጣ?” አሉት። እርሱም፥ “ሰውዬው ፌዝ እንደሚናገር አታውቁምን?” አላቸው።
ማቴዎስ 11:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፤ እነርሱም ‘ጋኔን አለበት’ አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሐንስ ከመብልና ከመጠጥ ተቈጥቦ በመምጣቱ፣ ‘ጋኔን አለበት’ ይሉታልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፤ እነርሱም ‘ጋኔን አለበት’ አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም መጥምቁ ዮሐንስ በመጣ ጊዜ እህል ሳይበላና የወይን ጠጅ ሳይጠጣ ቢመጣ፥ ‘ይህስ ጋኔን አለበት!’ አሉት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፥ እነርሱም፦ ጋኔን አለበት አሉት። |
ኢዩም ወደ ጌታው ብላቴኖች ወጣ፤ እነርሱም፥ “ደኅና ነውን? ይህ እብድ ለምን ወደ አንተ መጣ?” አሉት። እርሱም፥ “ሰውዬው ፌዝ እንደሚናገር አታውቁምን?” አላቸው።
ትንቢት የሚናገረውን ሰው ሁሉ፥ የሚለፈልፈውንም ሰው ሁሉ በግዞት ታኖረውና በፈሳሽም ታሰጥመው ዘንድ በእግዚአብሔር ቤት አለቃ እንድትሆን እግዚአብሔር በካህኑ በዮዳሄ ፋንታ ካህን አድርጎሃል።
የበቀል ወራት መጥቶአል፤ የፍዳም ወራት ደርሶአል፤ እስራኤልም እንደ አበደ ነቢይና ርኩስ መንፈስ እንደ አለበት ሰው ይታመማል፤ ከኀጢአትህና ከጠላትነትህ ብዛት የተነሣም ቍጣህን አበዛህ።
ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!
እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናልና የወይን ጠጅና የሚያሰክርም መጠጥ ሁሉ አይጠጣም፤ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮም መንፈስ ቅዱስ ይመላበታል።
አይሁድም እንዲህ አሉት፥ “አሁን ጋኔን እንዳለብህ ዐወቅን፤ አብርሃም ስንኳ ሞቶአል፤ ነቢያትም ሞተዋል፤ አንተ ግን ቃሌን የሚጠብቅ ለዘለዓለም ሞትን አይቀምስም ትላለህ።
ይህንም ስለ ራሱ ሲናገር ሀገረ ገዢው ፊስጦስ መለሰ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ፥ “ጳውሎስ ሆይ፥ ልታብድ ነውን? ብዙ ትምህርት እኮ ልብን ይነሣል” አለው።
ነገር ግን ለሌላ ሳስተምር፥ እኔ ለራሴ የተናቅሁ እንዳልሆን ሰውነቴን አስጨንቃታለሁ፥ ሥጋዬንም አስገዛዋለሁ።