ማቴዎስ 1:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓምም አብያን ወለደ፤ አብያም አሣፍን ወለደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰሎሞን ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓም አቢያን ወለደ፤ አቢያም አሣፍን ወለደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞን ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓም አቢያን ወለደ፤ አቢያም አሣፍን ወለደ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰሎሞን ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓም አቢያን ወለደ፤ አቢያ አሳፍን ወለደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰሎሞንም ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓምም አቢያን ወለደ፤ አቢያም አሣፍን ወለደ፤ |
እንዲህም ሆነ፤ የሮብዓም መንግሥት በጸናች ጊዜ፥ እርሱም በበረታ ጊዜ፥ የእግዚአብሔርን ሕግ ረሳ፤ እስራኤልም ሁሉ ከእርሱ ጋር ረሱ።
ክፉዎች ሰዎችና የሕግ ተላላፊዎች ልጆችም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ሮብዓም ሕፃን በነበረና በልቡ ድፍረት ባልነበረው ጊዜ፥ ሊቋቋመውም ባልቻለበት ጊዜ፥ በሰሎሞን ልጅ በሮብዓም ላይ በረታበት።
በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስቱም ከአሮን ልጆች ወገን ነበረች፤ ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ።