Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 12:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የሮ​ብ​ዓም መን​ግ​ሥት በጸ​ናች ጊዜ፥ እር​ሱም በበ​ረታ ጊዜ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ረሳ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ረሱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ሮብዓም መንግሥቱን ከመሠረተና ካጸና በኋላ፣ እርሱና እስራኤል ሁሉ የእግዚአብሔርን ሕግ ተዉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እንዲህም ሆነ፤ የሮብዓም መንግሥት በጸናች ጊዜ፥ እርሱም በበረታ ጊዜ፥ እርሱና እስራኤል ሁሉ የጌታን ሕግ ተዉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የሮብዓም መንግሥት በጽኑ በተመሠረተና ኀይል ባገኘ ጊዜ እርሱና እስራኤላውያን ሁሉ የእግዚአብሔርን ሕግ ተዉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እንዲህም ሆነ፤ የሮብዓም መንግሥት በጸናች ጊዜ፥ እርሱም በበረታ ጊዜ፥ እርሱና እስራኤል ሁሉ የእግዚአብሔርን ሕግ ተዉ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 12:1
22 Referencias Cruzadas  

በይ​ሁዳ ከተ​ሞች በተ​ቀ​መ​ጡት በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ግን ሮብ​ዓም ነገሠ።


የሰ​ሎ​ሞ​ንም ልጅ ሮብ​ዓም በይ​ሁዳ ነገሠ፤ ሮብ​ዓ​ምም ንጉሥ በሆነ ጊዜ የአ​ርባ አንድ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስሙን ያኖ​ር​ባት ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ በመ​ረ​ጣት ከተማ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዐሥራ ሰባት ዓመት ነገሠ፤ የእ​ና​ቱም ስም ናዕማ ነበረ፥ እር​ስ​ዋም አሞ​ና​ዊት ነበ​ረች።


መል​ሰ​ውም፦ ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ያወ​ጣ​ውን አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተው ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ስለ ተከ​ተሉ፥ ስለ ሰገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፥ ስለ አመ​ለ​ኩ​አ​ቸ​ውም፥ ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመ​ጣ​ባ​ቸው ይላሉ።” ያን​ጊ​ዜም ሰሎ​ሞን የፈ​ር​ዖ​ንን ልጅ ከዳ​ዊት ከተማ አው​ጥቶ በዚያ ወራት ለራሱ በሠ​ራው ቤት አስ​ገ​ባት።


ይሁ​ዳም ደግሞ እስ​ራ​ኤል ባደ​ረ​ጋት ሥር​ዐት ሄደ እንጂ የአ​ም​ላ​ኩን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ አል​ጠ​በ​ቀም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ተዉት።


ሦስት ዓመ​ትም በዳ​ዊ​ትና በሰ​ሎ​ሞን መን​ገድ ይሄድ ነበ​ርና ሦስት ዓመት የይ​ሁ​ዳን መን​ግ​ሥት አበ​ረቱ፤ የሰ​ሎ​ሞ​ን​ንም ልጅ ሮብ​ዓ​ምን አጸኑ።


ብል​ሃ​ተ​ኛም ሆነ፤ ልጆ​ቹ​ንም ሁሉ በይ​ሁ​ዳና በብ​ን​ያም ሀገር ሁሉ በም​ሽጉ ከተ​ሞች ሁሉ ከፋ​ፈ​ላ​ቸው፤ ብዙም ምግብ ሰጣ​ቸው፤ ብዙም ሚስ​ቶች ፈለ​ገ​ላ​ቸው።


“ለይ​ሁዳ ንጉሥ ለሰ​ሎ​ሞን ልጅ ለሮ​ብ​ዓም፥ በይ​ሁ​ዳና በብ​ን​ያ​ምም ላሉት ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ፦


ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጸና፤ ንጉ​ሥም ሆነ፤ ሮብ​ዓ​ምም በነ​ገሠ ጊዜ የአ​ርባ አንድ ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስሙን ያኖ​ር​ባት ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሀገር ሁሉ በመ​ረ​ጣት ከተማ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ዐሥራ ሰባት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም የአ​ሞን ሴት ንዑማ ነበ​ረች።


የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ትተው ባዕድ አም​ላ​ክ​ንና ጣዖ​ታ​ትን አመ​ለኩ፤ በዚ​ያም ወራት በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ቍጣ ወረደ።


ኀጢ​አ​ተኛ ወገ​ንና ዐመፅ የተ​ሞ​ላ​በት ሕዝብ፥ የክ​ፉ​ዎች ዘር፥ በደ​ለ​ኞች ልጆች ሆይ፥ ወዮ​ላ​ችሁ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተዋ​ች​ሁት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቅዱስ አስ​ቈ​ጣ​ች​ሁት።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ። በውኑ ለእ​ስ​ራ​ኤል ምድረ በዳ ወይስ የጨ​ለ​መች ምድር ሆን​ሁ​በ​ትን? ሕዝ​ቤስ ስለ ምን፦ እኛ አን​ገ​ዛ​ል​ህም፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ወደ አንተ አን​መ​ለ​ስም ይላል?


ኤፍ​ሬም እንደ ተና​ገረ በእ​ስ​ራ​ኤል ሥር​ዐ​ቱን ወሰደ፤ ለበ​ዓ​ልም አደ​ረ​ገው፤ ሞተም።


አንተን ለጥፋት፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ለማፍዋጫ እሰጥ ዘንድ የዘንበሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቃችኋል፥ በምክራቸውም ሄዳችኋል፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።


ያዕ​ቆብ በላ፤ ጠገ​በም፤ የተ​ወ​ደ​ደ​ውን ጥጋብ አቀ​ና​ጣው፤ ሰባ፥ ወፈረ፥ ሰፋ፤ የፈ​ጠ​ረ​ው​ንም እግ​ዚ​አ​ሔ​ርን ተወ፤ ከሕ​ይ​ወቱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ራቀ።


የወ​ለ​ደ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተውህ፤ ያሳ​ደ​ገ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ረሳ​ኸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ነ​ርሱ ላይ እንደ ማለ፥ ወደ ወጡ​በት ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ትከ​ፋ​ባ​ቸው ነበ​ረች፤ እጅ​ግም ተጨ​ነቁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos