አሳም በነገሠ በሠላሳ ዘጠነኛው ዓመት እግሩን ታመመ፤ ደዌውም ጸናበት፤ ነገር ግን በሕማሙ ጊዜ ባለ መድኀኒቶችን እንጂ እግዚአብሔርን አልፈለገም።
ሉቃስ 8:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ከእርሱ ጋር ሲሄድ ሰዎች ያጨናንቁት ነበር፤ ከዐሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም ይፈስሳት የነበረች ሴት መጣች፤ ገንዘብዋንም ሁሉ ለባለመድኀኒቶች ሰጥታ ጨርሳ ነበር፤ ነገር ግን ሊያድናት የቻለ ማንም አልነበረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐሥራ ሁለት ዓመት ደም ሲፈስሳት የኖረች አንዲት ሴት ነበረች፤ ሊፈውሳትም የቻለ ማንም አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዐሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፤ ያላትንም ንብረት ሁሉ ተጠቅማ ለባለመድኃኒቶች ብታውልም ማንም ሊፈውሳት አልተቻለውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐሥራ ሁለት ዓመት ሙሉ ደም እየመታት የምትሠቃይ አንዲት ሴት ነበረች፤ እርስዋም ያላትን ገንዘብ ሁሉ ለሐኪሞች በመክፈል ጨርሳ ማንም ሊያድናት አልቻለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፥ ትዳርዋንም ሁሉ ለባለመድኃኒቶች ከስራ ማንም ሊፈውሳት አልተቻለውም። |
አሳም በነገሠ በሠላሳ ዘጠነኛው ዓመት እግሩን ታመመ፤ ደዌውም ጸናበት፤ ነገር ግን በሕማሙ ጊዜ ባለ መድኀኒቶችን እንጂ እግዚአብሔርን አልፈለገም።
በያዘውም ስፍራ ሁሉ ይጥለዋል፤ አረፋም ይደፍቃል፤ ጥርሱንም ያፋጫል፤ ይደርቃልም፤ እንዲያወጡለትም ለደቀ መዛሙርትህ ነገርኋቸው፤ አልቻሉምም” አለው።
ይህቺ የአብርሃም ልጅ እነሆ፥ ሰይጣን ከአሰራት ዐሥራ ስምንት ዓመት ነው፤ እርስዋስ በሰንበት ቀን ከእስራቷ ልትፈታ አይገባምን?”
ወደ ምድርም በወረዱ ጊዜ ጋኔን ያደረበት ሰው ከከተማ ወጥቶ ተገናኘው፤ ልብሱንም ከጣለ ብዙ ዘመን ሆኖት ነበር፤ በመቃብር ብቻ ይኖር ነበር እንጂ ወደ ቤት አይገባም ነበር፤
አሁን ግን እንዴት እንደሚያይ ዐይኖቹንም ማን እንደ አበራለት አናውቅም፤ እርሱን ጠይቁት፤ ዐዋቂ ነውና፤ ስለ ራሱም መናገር ይችላልና።”
ከእናቱ ማኅፀንም ጀምሮ እግሩ ሽባ ሆኖ የተወለደ አንድ ሰው ነበር፤ ወደ መቅደስም ከሚገቡት ምጽዋት ይለምን ዘንድ ሁልጊዜ እየተሸከሙ መልካም በሚልዋት በመቅደስ ደጃፍ ያስቀምጡት ነበር።