Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 8:43 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 ዐሥራ ሁለት ዓመት ደም ሲፈስሳት የኖረች አንዲት ሴት ነበረች፤ ሊፈውሳትም የቻለ ማንም አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 ከዐሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፤ ያላትንም ንብረት ሁሉ ተጠቅማ ለባለመድኃኒቶች ብታውልም ማንም ሊፈውሳት አልተቻለውም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 ዐሥራ ሁለት ዓመት ሙሉ ደም እየመታት የምትሠቃይ አንዲት ሴት ነበረች፤ እርስዋም ያላትን ገንዘብ ሁሉ ለሐኪሞች በመክፈል ጨርሳ ማንም ሊያድናት አልቻለም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከእ​ርሱ ጋር ሲሄድ ሰዎች ያጨ​ና​ን​ቁት ነበር፤ ከዐ​ሥራ ሁለት ዓመ​ትም ጀምሮ ደም ይፈ​ስ​ሳት የነ​በ​ረች ሴት መጣች፤ ገን​ዘ​ብ​ዋ​ንም ሁሉ ለባ​ለ​መ​ድ​ኀ​ኒ​ቶች ሰጥታ ጨርሳ ነበር፤ ነገር ግን ሊያ​ድ​ናት የቻለ ማንም አል​ነ​በ​ረም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 ከአሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፥ ትዳርዋንም ሁሉ ለባለመድኃኒቶች ከስራ ማንም ሊፈውሳት አልተቻለውም።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 8:43
22 Referencias Cruzadas  

ታዲያ፣ ይህች ሴት የአብርሃም ልጅ ሆና ሳለች ዐሥራ ስምንት ዓመት ሙሉ በሰይጣን ታስራ ስትኖር፣ ከዚህ እስራት በሰንበት ቀን መፈታት አይገባትምን?”


በመንገድ ሲያልፍም ከተወለደ ጀምሮ ዐይነ ስውር የሆነ ሰው አየ።


በዚያም የድካም መንፈስ ዐሥራ ስምንት ዓመት ሙሉ አካለ ስንኩል ያደረጋት አንዲት ሴት ነበረች፤ እርሷም ከመጕበጧ የተነሣ ፈጽሞ ቀና ማለት አትችልም ነበር።


ኢየሱስ ከጀልባዋ ወደ ምድር በወረደ ጊዜ፣ አጋንንት ያደረበት አንድ ሰው ከከተማ ወጥቶ አገኘው፤ ይህ ሰው ለብዙ ጊዜ ልብስ ሳይለብስ፣ በቤትም ሳይኖር በመቃብር ቦታ ይኖር ነበር።


እስትንፋስ አፍንጫው ላይ ባለች በሰው አትታመኑ፤ ከቶ ምን የሚበጅ ነገር አለው!


አሳ በነገሠ በሠላሳ ዘጠነኛው ዓመት እግሮቹን ታመመ፤ ሕመሙ ቢጸናበትም እንኳ፣ በዚያ ሁሉ ሕመም የባለመድኀኒቶችን እንጂ የእግዚአብሔርን ርዳታ አልፈለገም።


በዚህ ታምር የተፈወሰውም ሰው ዕድሜው ከአርባ ዓመት በላይ ነበርና።


ወደ ቤተ መቅደስ ከሚገቡት ሰዎች ምጽዋት እንዲለምን፣ ሰዎች በየዕለቱ ተሸክመው “ውብ” በተባለው የቤተ መቅደስ መግቢያ በር ላይ የሚያስቀምጡት አንድ ከተወለደ ጀምሮ ሽባ የሆነ ሰው ነበረ፤


አሁን ግን እንዴት ማየት እንደ ቻለና ዐይኖቹን ማን እንደ ከፈተለት እኛ አናውቅም። ሙሉ ሰው ስለ ሆነ፣ ስለ ራሱ መናገር ይችላልና እርሱን ጠይቁት።”


በተነሣበት ጊዜ ሁሉ ይጥለዋል፤ ዐረፋ ይደፍቃል፤ ጥርሱንም ያፋጫል፤ ሰውነቱም ይደርቃል፤ ርኩስ መንፈሱን እንዲያስወጡት ደቀ መዛሙርትህን ጠየቅኋቸው፤ እነርሱ ግን አልቻሉም።”


በጠላት ላይ ድልን አቀዳጀን፤ የሰው ርዳታ ከንቱ ነውና።


እናንተ ግን፣ በሐሰት የምትለብጡ ናችሁ፤ ሁላችሁ የማትረቡ ሐኪሞች ሆናችኋል።


እነዚህ ሁሉ ከተረፈው ሀብታቸው ሰጡ፤ እርሷ ግን ከጕድለቷ ያላትን፣ መኖሪያዋን ሁሉ ሰጠች።”


ይህን ልመና ያቀረበው ዕድሜዋ ዐሥራ ሁለት ዓመት የሆነ አንዲት ልጅ ስለ ነበረችው ነው፤ እርሷ በሞት አፋፍ ላይ ነበረች። ወደዚያው እያመራ ሳለ፣ ሕዝቡ በመጋፋት እጅግ ያጨናንቀው ነበር።


እርሷም ከበስተኋላው ተጠግታ የልብሱን ጫፍ ነካች፤ የሚፈስሰው ደሟም ወዲያውኑ ቆመ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios