Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማርቆስ 12:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

44 ሁሉ ከትርፋቸው ጥለዋልና፤ ይህች ግን ከጕድለትዋ የነበራትን ሁሉ ትዳርዋን ሁሉ ጣለች፤” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

44 እነዚህ ሁሉ ከተረፈው ሀብታቸው ሰጡ፤ እርሷ ግን ከጕድለቷ ያላትን፣ መኖሪያዋን ሁሉ ሰጠች።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

44 እነዚህ ሁሉ ከተረፈው ሀብታቸው ሰጡ፤ እርሷ ግን በድህነት ዐቅሟ ያላትን ሁሉ አውጥታ ለመኖሪያ የሚሆናትን እንዳለ ሰጠች።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

44 ሌሎቹ ሁሉ የሰጡት ካላቸው ሀብት የተረፋቸውን ነው፤ እርስዋ ግን ድኻ ሆና ሳለች ምንም ሳታስቀር ያላትን ሁሉ ሰጠች።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

44 ሁሉ ከትርፋቸው ጥለዋልና፥ ይህች ግን ከጕድለትዋ የነበራትን ሁሉ ትዳርዋን ሁሉ ጣለች አላቸው።

Ver Capítulo Copiar




ማርቆስ 12:44
16 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል?


የተቻላትን አደረገች፤ አስቀድማ ለመቃብሬ ሥጋዬን ቀባችው።


“የሰ​ውን ነፍስ እንደ መው​ሰድ ነውና ወፍጮ ወይም መጅ ስለ መያዣ ማንም አይ​ው​ሰድ።


ከአ​መ​ን​ዝ​ሮች ጋር ገን​ዘ​ብ​ህን ሁሉ የጨ​ረሰ ይህ ልጅህ በተ​መ​ለሰ ጊዜ ግን የሰ​ባ​ውን ፍሪዳ አረ​ድ​ህ​ለት።’


ታናሹ ልጁም አባ​ቱን፦ ‘አባቴ ሆይ፥ ከገ​ን​ዘ​ብህ የሚ​ደ​ር​ሰ​ኝን ከፍ​ለህ ስጠኝ’ አለው፤ ገን​ዘ​ቡ​ንም ከፍሎ ሰጠው።


ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከእ​ርሱ ጋር ሲሄድ ሰዎች ያጨ​ና​ን​ቁት ነበር፤ ከዐ​ሥራ ሁለት ዓመ​ትም ጀምሮ ደም ይፈ​ስ​ሳት የነ​በ​ረች ሴት መጣች፤ ገን​ዘ​ብ​ዋ​ንም ሁሉ ለባ​ለ​መ​ድ​ኀ​ኒ​ቶች ሰጥታ ጨርሳ ነበር፤ ነገር ግን ሊያ​ድ​ናት የቻለ ማንም አል​ነ​በ​ረም።


ደቀ መዛሙርቱንም ጠርቶ “እውነት እላችኋለሁ፤ በመዝገብ ውስጥ ከሚጥሉት ሁሉ ይልቅ ይህች ድሀ መበለት አብልጣ ጣለች፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios