ሉቃስ 5:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻፎችና ፈሪሳውያንም፥ “የሚሳደብ ይህ ማን ነው? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኀጢአትን ማስተስረይ ማን ይችላል?” ብለው ያስቡ ጀመር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጸሐፍትና ፈሪሳውያንም፣ “አምላክን በመሳደብ እንዲህ የሚናገር ይህ ማን ነው? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኀጢአትን ሊያስተሰርይ ማን ይችላል?” ብለው ያስቡ ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጻፎችና ፈሪሳውያንም፦ “ስድብን የሚሰነዝር ይህ ማን ነው? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በስተቀር ሌላ ማን ኃጢአትን ሊያስተሰርይ ይችላል?” እያሉ ያስቡ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን “በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ይህ ማነው? ኃጢአትን የሚደመስስ እግዚአብሔር ብቻ ነው እንጂ ሌላ ማነው?” እያሉ ያስቡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጻፎችና ፈሪሳውያንም፦ ይህ የሚሳደብ ማን ነው? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኃጢአት ሊያስተሰርይ ማን ይችላል? ብለው ያስቡ ጀመር። |
“ኑና እንዋቀስ” ይላል እግዚአብሔር፤ ኀጢአታችሁ እንደ አለላ ቢሆን እንደ በረዶ አነጻዋለሁ፤ እንደ ደምም ቢቀላ እንደ ባዘቶ አጠራዋለሁ።
የእግዚአብሔርንም ስም ጠርቶ የሚሰድብ ሁሉ ፈጽሞ ይገደል፤ ማኅበሩም ሁሉ በድንጋይ ይውገሩት፤ መጻተኛ ወይም የሀገር ልጅ ቢሆን፥ የእግዚአብሔርን ስም ጠርቶ ቢሳደብ ይገደል።
በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ “ተሳድቦአል፤ እንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ስለ ምን ያስፈልገናል? እነሆ፥ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል፤ ምን ይመስላችኋል?” አለ።
እንግዲህ ለንስሓ የሚያበቃችሁን ሥራ ሥሩ፤ አብርሃም አባታችን አለን በማለት የምታመልጡ አይምሰላችሁ፤ እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆችን ማስነሣት እንደሚችል እነግራችኋለሁ።
ከዚህም በኋላ፥ ከዕለታት በአንድ ቀን ሲያስተምራቸው እንዲህ ሆነ፤ ከገሊላና ከይሁዳ መንደሮች፥ ከኢየሩሳሌምም የመጡ ፈሪሳውያንና የኦሪት መምህራን ነበሩ፤ እርሱም ይፈውስ ዘንድ የእግዚአብሔር ኀይል ነበረ።
አይሁድም፥ “አንተ፥ ሰው ስትሆን ራስህን እግዚአብሔርን ታደርጋለህና፤ ስለ መሳደብህ ነው እንጂ ስለ መልካም ሥራህስ አንወግርህም” አሉት።