ለሕዝቡም ሁሉ ለእስራኤል ወገን ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ለወንዱም፥ ለሴቱም ለእያንዳንዱ አንዳንድ እንጀራ፥ አንዳንድም የሥጋ ቍራጭ፥ አንዳንድም ጽዋዕ ወይን አከፋፈለ። ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ ወደ ቤቱ ሄደ።
ሉቃስ 14:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በበዓል ምሳ በምታደርግበት ጊዜ ድሆችንና ጦም አዳሪዎችን፥ ዕውሮችን፥ እጅና እግርም የሌላቸውን ጥራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ግብዣ ባዘጋጀህ ጊዜ ድኾችን፣ አካለ ስንኩሎችን፣ ሽባዎችንና ዐይነ ስውሮችን ጥራ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ግብዣ ባሰናዳህ ጊዜ ድሆችንና ጉንድሾችን አንካሶችንም ዐይነ ስውሮችንም ጥራ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ድኾችን፥ አካለ ስንኩሎችን፥ ሽባዎችን፥ ዕውሮችንም ሰዎች ጥራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ግብዣ ባደረግህ ጊዜ ድሆችንና ጕንድሾችን አንካሶችንም ዕውሮችንም ጥራ፤ |
ለሕዝቡም ሁሉ ለእስራኤል ወገን ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ለወንዱም፥ ለሴቱም ለእያንዳንዱ አንዳንድ እንጀራ፥ አንዳንድም የሥጋ ቍራጭ፥ አንዳንድም ጽዋዕ ወይን አከፋፈለ። ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ ወደ ቤቱ ሄደ።
ንጉሡ ሕዝቅያስም ስለ ቍርባን ሺህ ወይፈኖችንና ሰባት ሺህ በጎችን ለይሁዳና ለጉባኤው ሰጥቶ ነበር፤ አለቆቹም ሺህ ወይፈኖችንና ዐሥር ሺህ በጎችን ለጉባኤው ሰጥተው ነበር፤ ከካህናቱ እጅግ ብዙ ተቀድሰው ነበርና።
እርሱም፥ “ሂዱ፤ የሰባውንም ብሉ፤ ጣፋጩንም ጠጡ፤ ለእነዚያም ምንም ለሌላቸው እድል ፈንታቸውን ላኩ፤ ዛሬ ለጌታችን የተቀደሰ ቀን ነው፤ እግዚአብሔርም ኀይላችን ነውና አትዘኑ” አላቸው።
ለድሃ የሚራራ እርሱ ይበላል እንጀራውን ለድሃ ሰጥቶአልና። ለሰጠው ሀብታምም የሚከፍል አይደለምና። መማለጃን የሰጠ ሰው ድል መንሣትንና ሞገስን ያገኛል፥ ነገር ግን የተቀበለውን ነፍስ ያጠፋል።
ከምግብህም ለተራበ ብታካፍል፥ የተራበች ሰውነትንም ብታጠግብ፥ ያንጊዜ ብርሃንህ በጨለማ ይወጣል፤ ጨለማህም እንደ ቀትር ይሆናል።
ለተራበውም እንጀራህን አጥግበው፤ ድሆችን ወደ ቤትህ አስገብተህ አሳድራቸው፤ የተራቈተውንም ብታይ አልብሰው፤ ከሥጋ ዘመድህ አትሸሽግ።
ብዙ ሕዝብም አንካሶችን፥ ዕውሮችንም፥ ድዳዎችንም፥ ጉንድሾችንም፥ ሌሎችንም ብዙ ይዘው ወደ እርሱ ቀረቡ በኢየሱስም እግር አጠገብ አስቀመጡአቸው፤ ፈወሳቸውም፤
የጠራውንም እንዲህ አለው፥ “በበዓል ምሳ ወይም ራት በምታደርግበት ጊዜ ወዳጆችህንና ወንድሞችህን፥ ዘመዶችህንና ጎረቤቶችህን፥ ባለጸጎች ባልንጀሮችህንም አትጥራ፤ እነርሱም ይጠሩሃልና፤ ብድርም ይሆንብሃልና።
አገልጋዩም ተመልሶ ለጌታው ይህንኑ ነገረው፤ ያንጊዜም ባለቤቱ ተቈጣ፤ አገልጋዩንም፦ ፈጥነህ ወደ አደባባይና ወደ ከተማው ጐዳና ሂድ፤ ድሆችንና ጦም አዳሪዎችን፥ ዕውሮችንና አንካሶችን ወደዚህ አምጣልኝ አለው።
ጴጥሮስም ተነሥቶ አብሮአቸው ሄደ፤ በደረሰም ጊዜ ወደ ሰገነት አወጡት፤ ባልቴቶችም ሁሉ ወደ እርሱ መጥተው በፊቱ ቆሙ፤ ያለቅሱላትም ነበር፤ ዶርቃስም በሕይወት ሳለች የሠራችውን ቀሚሱንና መጐናጸፊያውን አሳዩት።
ሌዋዊዉም፥ ከአንተ ጋር ክፍልና ርስት የለውምና፥ በከተማህ ውስጥ ያለ መጻተኛ፥ ድሃ-አደግም፥ መበለትም መጥተው ይበላሉ፤ ይጠግባሉም፤ ይኸውም አምላክህ እግዚአብሔር በምታደርገው በእጅህ ሥራ ሁሉ ይባርክህ ዘንድ ነው።
አንተ፥ ወንድ ልጅህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባሪያህና ሴት ባሪያህ፥ በሀገርህም ውስጥ ያለው ሌዋዊ፥ በመካከልህም ያሉ መጻተኛና ድሃ-አደግ፥ መበለትም አምላክህ እግዚአብሔር በዚያ ስሙ ይጠራበት ዘንድ በሚመርጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላችሁ።
አንተም፥ ወንድ ልጅህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባሪያህና ሴት ባሪያህ፥ በሀገርህም ውስጥ ያለ ሌዋዊና መጻተኛ፥ ድሃ-አደግና መበለትም በበዓልህ ደስ ይበላችሁ።
እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ የማይነቀፍ፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ ልከኛ፥ ራሱን የሚገዛ፥ እንደሚገባው የሚሠራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር የሚበቃ፥
ልጆችን በማሳደግ፥ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት፥ በጎንም ሥራ ሁሉ በመከተል፥ ይህን መልካም ሥራ በማድረግ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።