Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 14:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ድሃን የሚያስጨንቅ ፈጣሪውን ያስቈጣዋል፤ ፈጣሪውን የሚያከብር ግን ለድሃ ምሕረትን ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ድኾችን የሚያስጨንቅ ፈጣሪያቸውን ይንቃል፤ ለተቸገሩ የሚራራ ሁሉ ግን አምላክን ያከብራል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ድሀን የሚያስጨንቅ ፈጣሪውን ይሰድባል፥ ለድሀ ምሕረትን የሚያደርግ ግን ያከብረዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ድኾችን ማስጨነቅ ፈጣሪን መናቅ ነው፤ ለድኾች ቸርነትን ማድረግ ግን እግዚአብሔርን እንደ ማክበር ይቈጠራል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 14:31
19 Referencias Cruzadas  

ባለ ጠጋና ድሃ በአንድነት ተገናኙ፤ ሁለቱንም እግዚአብሔር ፈጠራቸው።


ድሃን የሚቀማ ገንዘቡን ብዙ ያደርግለታል፥ በችግሩ ጊዜም ለባለጠጋ ይሰጣል።


በድሃ የሚያላግጥ ፈጣሪውን ያነሣሣዋል፥ በሚጠፋም ላይ ደስ የሚለው ከፍርድ አይነጻም፥ የሚራራ ግን ምሕረትን ያገኛል።


ለድሃ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ እንደ ስጦታውም መልሶ ይከፍለዋል።


እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።


ከፍ ካለው በላይ ከፍ ያለ ይጠ​ብ​ቅ​ሃ​ልና፥ ከእ​ነ​ር​ሱም በላይ ደግሞ ሌሎች ከፍ ይላ​ሉና በሀ​ገሩ ድሃ ሲበ​ደል፥ ፍር​ድና ጽድ​ቅም ሲነ​ጠቅ ብታይ በሥ​ራው አታ​ድ​ንቅ።


እኔ ግን በቸ​ር​ነ​ትህ ታመ​ንሁ፥ ልቤም በማ​ዳ​ንህ ደስ ይለ​ዋል።


ድሆች ግን ዘወ​ትር አብ​ረ​ዋ​ችሁ አሉ፤ ዘወ​ት​ርም ታገ​ኙ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ በወ​ደ​ዳ​ች​ሁም ጊዜ መል​ካም ታደ​ር​ጉ​ላ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ እኔን ግን ዘወ​ትር የም​ታ​ገ​ኙኝ አይ​ደ​ለም።”


ድሃውን የሚንቅ ኀጢአትን ይሠራል፤ ለድሃ የሚራራ ግን ብፁዕ ነው።


እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና ሰው ባል​ን​ጀ​ራ​ውን አያ​ስ​ጨ​ንቅ፤ ነገር ግን አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍራ።


“ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ ወይም በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ከአ​ሉት መጻ​ተ​ኞች ድሃና ችግ​ረኛ የሆ​ነ​ውን ምን​ደኛ ደመ​ወ​ዙን አት​ከ​ል​ክ​ለው፤


ደካ​ሞ​ችን ከእ​ው​ነት መን​ገድ ያወ​ጣሉ፤ የም​ድ​ርም የዋ​ሃን ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ይሸ​ሸ​ጋሉ።


“ከአ​ንተ ጋር ያለው ወን​ድ​ምህ ቢደ​ኸይ፥ እጁም በአ​ንተ ዘንድ ቢደ​ክም እንደ እን​ግ​ዳና እንደ መጻ​ተኛ ትረ​ዳ​ዋ​ለህ፤ ከአ​ን​ተም ጋር ይኑር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios