የእግዚአብሔርንም ታቦት ከቂርያትይዓሪም ያመጡ ዘንድ ዳዊት እስራኤልን ሁሉ ከግብፅ ዳርቻ ጀምሮ እስከ ኤማት መግቢያ ድረስ ሰበሰበ።
ዘሌዋውያን 8:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማኅበሩንም ሁሉ ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ሰብስባቸው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማኅበሩን በሙሉ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሰብስብ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማኅበሩንም ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሰብስብ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም የእስራኤልን ሕዝብ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሰብስብ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማኅበሩንም ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሰብስባቸው። |
የእግዚአብሔርንም ታቦት ከቂርያትይዓሪም ያመጡ ዘንድ ዳዊት እስራኤልን ሁሉ ከግብፅ ዳርቻ ጀምሮ እስከ ኤማት መግቢያ ድረስ ሰበሰበ።
የይሁዳም ጉባኤ ሁሉ ፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ፥ ከእስራኤልም የመጡ ጉባኤ ሁሉ፥ ከእስራኤልም ሀገር የመጡትና በይሁዳ የኖሩት እንግዶች ደስ አላቸው።
በዚያ ጊዜም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን ያወጡ ዘንድ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና የነገድ አለቆችን ሁሉ፥ የእስራኤልንም ልጆች አባቶች ቤቶች መሳፍንት ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።
ንጉሡም ሰሎሞንና የእስራኤል ማኅበር ሁሉ፥ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ በአንድነት በታቦቷ ፊት ሆነው ከብዛት የተነሣ የማይቈጠሩትንና የማይመጠኑትን በጎችና በሬዎች ይሠዉ ነበር።
ሰባተኛውም ወር በደረሰ ጊዜ የእስራኤል ልጆች በከተሞቻቸው ነበሩ። ሕዝቡም ሁሉ በውኃው በር ፊት ወዳለው አደባባይ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ፤ እግዚአብሔርም ለእስራኤል ያዘዘውን የሙሴን ሕግ መጽሐፍ ያመጣ ዘንድ ጸሓፊውን ዕዝራን ነገሩት።
የሚያነጻውም ካህን እነዚህን ነገሮች፥ የሚነጻውንም ሰው በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርባቸዋል።
“አሮንን፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹን፥ ልብሱንም፥ የቅብዐቱንም ዘይት፥ ለኀጢአት መሥዋዕትም የሆነውን ወይፈን፥ ሁለቱንም አውራ በጎች፥ የቂጣውንም እንጀራ መሶብ ውሰድ፤
“ይህችን በትርህን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮንም ማኅበሩን ሰብስቡ፤ ዐለቷንም በፊታቸው እዘዟት፤ ውኃ ትሰጣለች፤ ከድንጋይዋም ውኃ ታወጡላቸዋላችሁ፤ እንዲሁም ማኅበሩን፥ ከብቶቻቸውንም ታጠጡላቸዋላችሁ።”