ዘሌዋውያን 7:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቍርባኑም ሁሉ የእግዚአብሔርን ድርሻ ከእነርሱ አንዱን ያነሣል። እርሱም የደኅንነትን መሥዋዕት ደም ለሚረጨው ካህን ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእያንዳንዱም ዐይነት አንዳንድ አንሥቶ ለእግዚአብሔር የተለየ ቍርባን በማድረግ ያቅርብ፤ ይህም የኅብረት መሥዋዕቱን ደም ለሚረጨው ካህን ይሰጥ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታ እንደ ስጦታ አድርጎ አንድ ኅብስት ከእያንዳንዱ ቁርባን ያቀርባል። ከእርሱም የቀረው የአንድነትን መሥዋዕት ደም ለሚረጨው ካህን ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእያንዳንዱ የኅብስት ዐይነት አንዱን ክፍል ለእግዚአብሔር የተለየ መባ አድርጎ ያቀርባል፤ ያም መባ የእንስሳውን ደም ወስዶ በመሠዊያው ጐን የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ ለረጨው ካህን ድርሻ ይሁን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከቍርባኑም ሁሉ ለእግዚአብሔር የማንሣት ቍርባን እንዲሆን ከእነርሱ አንዱን ያነሣል። እርሱም የደኅንነትን መሥዋዕት ደም ለሚረጨው ካህን ይሆናል። |
የእስራኤል ልጆች ለእግዚአብሔር የሚለዩትን የተቀደሰውን መባ ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ሰጥቼሃለሁ፤ ይህም ለአንተ ከአንተም በኋላ ለዘርህ በእግዚአብሔር ፊት የዘለዓለም ሕግና የሁልጊዜ ቃል ኪዳን ነው።”