እናንተ የእግዚአብሔርን ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፤ እልፍ በሉ፤ ከዚያ ውጡ፤ ርኩስን ነገር አትንኩ፤ ከመካከልዋ ውጡ፤ ራሳችሁን ለዩ።
ዘሌዋውያን 5:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርኩስ ነገርን፥ የሞተውን፥ አውሬ የነከሰውን፥ ወይም የበከተ፥ ወይም የሚንቀሳቀስ የእንስሳን በድን የነካ፥ ከእርሱም ያነሣ ሰው ቢኖር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ማንኛውም ሰው ሳያውቅ በሥርዐቱ መሠረት የተከለከለውን ርኩስ ነገር ቢነካ፣ ይኸውም፦ የረከሰ የአውሬ በድን ወይም የረከሰ የቤት እንስሳ በድን ወይም በደረቱ እየተሳበ የሚንቀሳቀሰውን የረከሰ ፍጥረት በድን ቢነካ ይህ ሰው ረክሷል፤ በደለኛም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም ሰው ማንኛውንም ርኩስ ነገር ማለትም የረከሰ አውሬ በድን፥ ወይም የረከሰ ከብት በድን፥ ወይም በደረቱ እየተሳበ የሚርመሰመስ የረከሰ ፍጥረት በድን ሳይታወቀው ቢነካ፥ እርሱ ርኩስ ይሆናል፤ በደለኛም ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው ባለማወቅ ማናቸውንም ርኩስ ነገር ለምሳሌ የአውሬ፥ የቤት እንስሳ ወይም በደረቱ እየተሳበ የሚንቀሳቀስ ፍጥረት በድን ቢነካ፥ ያደረገውን ስሕተት ካወቀበት ጊዜ አንሥቶ በደል ይሆንበታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማናቸውም ሰው ሳይታወቀው ርኩስ ነገር ቢነካ፥ የረከሰም አውሬ በድን፥ ወይም የረከሰ ከብት በድን፥ ወይም የረከሰ የተንቀሳቀሰ እንስሳ በድን ቢሆን፥ እርሱም ርኩስ ቢሆን ነገሩ በታወቀው ጊዜ በደል ይሆንበታል፤ |
እናንተ የእግዚአብሔርን ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፤ እልፍ በሉ፤ ከዚያ ውጡ፤ ርኩስን ነገር አትንኩ፤ ከመካከልዋ ውጡ፤ ራሳችሁን ለዩ።
“የእስራኤል ማኅበር ሁሉ ቢስቱ፥ ነገሩም ከማኅበሩ ዐይን ቢሸሸግ፥ እግዚአብሔርም አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን ቢተላለፉ፤
“ሰው ባለማወቅ ኀጢአት ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን ቢተላለፍ፥ ቢታወቀው፥ ኀጢአት ስለሆነችበትም ንስሓ ቢገባ፥
ሰው ሳያስብ ክፉን ወይም መልካምን ያደርግ ዘንድ ሳያስብ በከንፈሩ ተናግሮ ቢምል፥ ሳያስብ የማለውም ከዚህ ባንዱ ነገር ቢሆን፥ በታወቀው ጊዜ ከዚህ ነገር በአንዱ በደለኛ ይሆናል።
ከርኩስ ሁሉ፥ ወይም ከረከሰው ሰው፥ ወይም ንጹሕ ካልሆነው እንስሳ የነካች ሰውነት፥ ለእግዚአብሔር ከሆነው ከደኅንነት መሥዋዕት ሥጋ ብትበላ፥ ያች ሰውነት ከሕዝብዋ ተለይታ ትጥፋ።”
እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ወዮላችሁ! ሰዎች ሳያውቁ በላዩ እንደሚመላለሱበት እንደ ተሰወረ መቃብር ናችሁና።”
ስለዚህም “ከመካከላቸው ተለይታችሁ ውጡ፤ ከእነርሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩሳንም አትቅረቡ፥ እኔም እቀበላችኋለሁ።
እርያም፥ ሰኰናው ስለተሰነጠቀ፥ ጥፍሩም ከሁለት ስለተከፈለ፥ ነገር ግን ሰለማያመሰኳ፥ እርሱ ለእናንተ ርኩስ ነው፤ ሥጋዉን አትብሉ፤ በድኑንም አትንኩ።