የእግዚአብሔርንም ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለላት ድንኳን ውስጥ በስፍራዋ አኖሩአት፤ ዳዊትም የሚቃጠልና የሰላም መሥዋዕትን በእግዚአብሔር ፊት አሳረገ።
ዘሌዋውያን 3:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከደኅንነቱም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል፤ ስቡን፥ እስከ ጀርባውም ድረስ የተቈረጠ ሙሉ ላቱን፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኅብረት መሥዋዕቱ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ እንከን የሌለው መሥዋዕት ያምጣ፤ ሥቡን፣ እስከ ጀርባ ዐጥንቱ ድረስ የተቈረጠ ላቱን በሙሉ፣ የሆድ ዕቃውን የሸፈነውን ሥብ፣ ከሆድ ዕቃው ጋራ የተያያዘውን ሥብ ሁሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰላሙም መሥዋዕት ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጎ የሚያቀርበው፤ ስቡን፥ እስከ ጀርባውም ድረስ የተቈረጠ ላቱን ሁሉ፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ ከቀረበው ከአንድነቱ መሥዋዕት ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆነው የሚቀርቡት ስቡና ከጀርባ አጥንቱ ሥር የተቈረጠው ላቱ በሙሉ፥ የሆድ ዕቃው የሚሸፈንበት ስብ ሁሉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከደኅንነቱም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን አድርጎ ያቀርባል፤ ስቡን፥ እስከ ጀርባውም ድረስ የተቈረጠ ላቱን ሁሉ፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥ |
የእግዚአብሔርንም ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለላት ድንኳን ውስጥ በስፍራዋ አኖሩአት፤ ዳዊትም የሚቃጠልና የሰላም መሥዋዕትን በእግዚአብሔር ፊት አሳረገ።
ሰሎሞንም ነቃ፤ እነሆም፥ ሕልም ነበረ፤ ተነሥቶም ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፤ በጽዮንም በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ቆመ፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አሳረገ፤ የደኅንነትንም መሥዋዕት አቀረበ፤ ለአገልጋዮቹም ሁሉ ታላቅ ግብዣ አደረገ።
ንጉሡ ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ስለ ሰላም መሥዋዕት ሃያ ሁለት ሺህ በሬዎችንና መቶ ሃያ ሺህ በጎችን አቀረበ። ንጉሡና የእስራኤል ልጆች ሁሉ እንዲሁ የእግዚአብሔርን ቤት ቀደሱ፤ አከበሩም።
በእግዚአብሔር ፊት ያለው የናሱ መሠዊያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን የሰላሙንም መሥዋዕት ስብ ይይዝ ዘንድ ታናሽ ስለ ነበረ፥ በዚያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን፥ የሰላሙንም መሥዋዕት ስብ አሳርጎአልና በእግዚአብሔር ቤት ፊት የነበረውን የአደባባዩን መካከል ንጉሡ በዚያ ቀን ቀደሰ።
የእግዚአብሔርንም ታቦት ይዘው ገቡ፤ ዳዊትም በተከለላት ድንኳን ውስጥ አኖሩአት፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕትም በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ።
የበጉንም ስብ፥ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱንም ኵላሊቶች፥ በላያቸውም ላይ ያለውን ስብ፥ የቀኙንም ወርች ትወስዳለህ፤ የሚቀደሱበት ነውና።
እግዚአብሔር ከግርፋቱ ያነጻው ዘንድ ፈቀደ፤ ስለ ኀጢአት መሥዋዕትን ብታቀርቡ ሰውነታችሁ ረዥም ዕድሜ ያለውን ዘር ታያለች።
ስለዚህ የእስራኤል ልጆች በሜዳ የሚያርዱትን መሥዋዕታቸውን ወደ እግዚአብሔር ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ያመጡታል፤ ወደ ካህኑም አምጥተው ለእግዚአብሔር ለድኅነት መሥዋዕት ይሠዉታል።
ስቡንና ላቱን፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥ የጉበቱንም መረብ፥ ሁለቱንም ኵላሊቶች፥ ስባቸውንም፥ ቀኝ ወርቹንም ወሰደ፤
የበሬውንና የአውራውንም በግ ስብ፥ ላቱንም፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ ሁለቱን ኵላሊቶቹንም፥ በላያቸውም ያለውን ስብ፥ የጉበቱንም መረብ አመጡለት።
የደኅንነትም መሥዋዕት ከብት ሁሉ፥ ሃያ አራት ጊደሮች፥ ስድሳም አውራ በጎች፥ ስድሳም አውራ ፍየሎች፥ ስድሳም ነውር የሌለባቸው የአንድ ዓመት እንስት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። መሠዊያው ከተቀባ በኋላ ለመቀደሻው የቀረበ ቍርባን ይህ ነበረ።
በፊቴም ወደ ጌልገላ ትወርዳለህ፤ እኔም እነሆ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀርብ ዘንድ፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት እሠዋ ዘንድ ወደ አንተ እወርዳለሁ፤ እኔ ወደ አንተ እስክመጣና የምታደርገውን እስከምነግርህ ድረስ ሰባት ቀን ትቈያለህ።”