ኢዮአስም ካህናቱን፥ “ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚገባውን የተቀደሰውን ገንዘብ ሁሉ፥ ስለ ነፍሱም ዋጋ የሚያቀርበውን ገንዘብ፥ በልባቸውም ፈቃድ ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚያመጡትን ገንዘብ ሁሉና፥
ዘሌዋውያን 27:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለወንድ ከሃያ ዓመት ጀምሮ እስከ ስድሳ ዓመት ድረስ እንደ መቅደሱ ሚዛን ግምቱ አምሳ የብር ዲድርክም ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕድሜው ከሃያ እስከ ስድሳ ዓመት ለሆነ ወንድ፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት፣ ግምቱ ዐምሳ ጥሬ ሰቅል ብር ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለወንድ ከሃያ ዓመት ጀምሮ እስከ ስልሳ ዓመት ድረስ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ግምትህ ኀምሳ የብር ሰቅል ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቤተ መቅደሱስ በታወቀው ሚዛን ልክ ዕድሜው ከኻያ እስከ ሥልሳ ለሆነ ወንድ 600 ግራም የሚመዝን ጥሬ ብር ይሁን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለወንድ ከሃያ ዓመት ጀምሮ እስከ ስድሳ ዓመት ድረስ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ግምቱ አምሳ የብር ሰቅል ይሁን። |
ኢዮአስም ካህናቱን፥ “ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚገባውን የተቀደሰውን ገንዘብ ሁሉ፥ ስለ ነፍሱም ዋጋ የሚያቀርበውን ገንዘብ፥ በልባቸውም ፈቃድ ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚያመጡትን ገንዘብ ሁሉና፥
ይቈጠሩ ዘንድ የሚያልፉት ሁሉ የሚሰጡት ይህ ነው፤ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን የሰቅል ግማሽ ይሰጣል። ሰቅሉም ሃያ አቦሊ ነው፤ የሰቅሉም ግማሽ ለእግዚአብሔር ቍርባን ነው።
የተሰጠው ወርቅ ሁሉ፥ ለድንኳኑ ሥራ ሁሉ የተደረገው ወርቅ፥ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ሃያ ዘጠኝ መክሊት ሰባት መቶ ሠሳሳ ሰቅል ነበረ።
“ሰውም ለእግዚአብሔር ቅዱስ ይሆን ዘንድ ቤቱን ቢቀድስ፥ ካህኑ መልካም ወይም ክፉ እንደ ሆነ ይገምተዋል፤ ካህኑም እንደሚገምተው መጠን እንዲሁ ይቆማል።
“ሰው ቢዘነጋ፥ ሳያውቅም ለእግዚአብሔር በተቀደሰው በማናቸውም ነገር ኀጢአትን ቢሠራ፥ ለበደል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ከመንጋዉ ነውር የሌለበትን እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን በብር ሰቅል የተገመተውን አውራ በግ ለበደል መሥዋዕት ያቀርባል።
ስለ በደል መሥዋዕትም ከመንጋው ነውር የሌለበትን፥ ዋጋው እንደ በደሉ የተገመተውን አውራ በግ ለእግዚአብሔር ያምጣ።።