ደግሞም ገጸ ኅብስት፥ ስስ ቂጣም ቢሆን፥ በምጣድም ቢጋገር፥ ቢለወስም ለእህል ቍርባን በሆነው በመልካሙ ዱቄት በመስፈሪያና በልክ ሁሉ ያገለግሉ ዘንድ ሹሞአቸው ነበር።
ዘሌዋውያን 24:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ፊት ሁል ጊዜ በሰንበት ቀን ሁሉ ያድርጉት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ የዘለዓለም ቃል ኪዳን ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኅብስቱ የእስራኤልን ሕዝብ ይወክል ዘንድ ዘወትር በየሰንበቱ በእግዚአብሔር ፊት ይደርደር፤ ይህም የዘላለም ቃል ኪዳን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ እስራኤል ልጆች የዘለዓለም ቃል ኪዳን እንዲሆን በጌታ ፊት ሁልጊዜ በሰንበት ቀን ሁሉ በተርታ ያዘጋጀዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮን ስለ እስራኤል ሕዝብ ሆኖ ኅብስቱን በየሰንበቱ ለሁልጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ያኖረዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ በሰንበት ቀን ሁሉ በተርታ ያድርገው፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ የዘላለም ቃል ኪዳን ነው። |
ደግሞም ገጸ ኅብስት፥ ስስ ቂጣም ቢሆን፥ በምጣድም ቢጋገር፥ ቢለወስም ለእህል ቍርባን በሆነው በመልካሙ ዱቄት በመስፈሪያና በልክ ሁሉ ያገለግሉ ዘንድ ሹሞአቸው ነበር።
በየጥዋቱና በየማታውም ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ጣፋጩን ዕጣን ያሳርጋሉ፤ የገጹንም ኅብስት በንጹሕ ገበታ ላይ፥ የወርቁን መቅረዝና ቀንዲሎቹንም ማታ ማታ እንዲያበሩ ያዘጋጃሉ፤ እኛም የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንጠብቃለን፤ እናንተ ግን ትታችሁታል።
እነሆ፥ ለእስራኤል ለዘለዓለም እንደ ታዘዘው በእግዚአብሔር ፊት የጣፋጩን ሽቱ ዕጣን ለማጠን፥ የገጹንም ኅብስት ለማኖር፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በጥዋትና በማታ፥ በሰንበታቱም፥ በመባቻዎቹም፥ በአምላካችንም በእግዚአብሔር በዓላት ለማቅረብ እኔ ልጁ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤት እሠራለሁ፤ እርሱንም እቀድሳለሁ።
ስለ አምላካችንም ቤት አገልግሎት፥ ስለ ኅብስተ ገጽም፥ ዘወትርም በሰንበትና በመባቻ ስለ ማቅረብ ስለ እህሉ ቍርባንና ስለሚቃጠለው መሥዋዕት፥ ስለ በዓላትም፥ ስለ ተቀደሱትም ነገሮች፥ ለእስራኤልም ስለሚያስተሰርየው ስለ ኀጢአት መሥዋዕት፥
በኅብስተ ገጹ ገበታ ላይም ሰማያዊውን መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤ በእርሱም ላይ ወጭቶቹን፥ ጭልፋዎቹንም፥ ጽዋዎቹንም፥ ለማፍሰስም መቅጃዎቹን ያድርጉበት፤ ሁልጊዜም የሚኖር ኅብስት በእርሱ ላይ ይሁን።
በዚያም ቀን ከሳኦል አገልጋዮች አንድ ሰው በኔሴራ አቅራቢያ በዚያ በእግዚአብሔር ፊት ነበር፤ ስሙም ሶርያዊው ዶይቅ ነበረ፤ የሳኦልም በቅሎዎች ጠባቂ ነበረ።