“ከጥሩ ወርቅም የወርቅ ቅጠል ሥራ፤ በእርሱም እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገህ፦ ቅድስና ለእግዚአብሔር የሚል ትቀርጽበታለህ።
ዘሌዋውያን 21:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአምላኩም ቅባት ዘይት ቅዱስነት በላዩ ነውና ከመቅደስ አይውጣ፤ የአምላኩንም ቅዱስ ስም አያርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተቀደሰበት የአምላኩ የቅብዐት ዘይት በላዩ ስለ ሆነ የአምላኩን መቅደስ ትቶ በመሄድ መቅደሱን አያርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚቀድስውም የአምላኩ የቅባዓት ዘይት በእርሱ ላይ ነውና ከመቅደስ አይውጣ፥ የአምላኩንም መቅደስ አያርክስ፤ እኔ ጌታ ነኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእኔ የአምላኩ የክህነት ቅድስና በእርሱ ላይ ስላለ ከመቅደስ ወጥቶ የአምላኩን መቅደስ አያርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአምላኩም ቅባት ዘይት ቅዱስነት በላዩ ነውና ከመቅደስ አይውጣ፥ የአምላኩንም መቅደስ አያርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
“ከጥሩ ወርቅም የወርቅ ቅጠል ሥራ፤ በእርሱም እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገህ፦ ቅድስና ለእግዚአብሔር የሚል ትቀርጽበታለህ።
የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን፥ ለዕውራንም ማየትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።
የእግዚአብሔር የቅብዐት ዘይት በላያችሁ ነውና እንዳትሞቱ ከምስክሩ ድንኳን ደጃፍ አትውጡ” አላቸው። ሙሴም እንዳዘዛቸው አደረጉ።
ሙሴም ከቅብዐቱ ዘይትና በመሠዊያው ላይ ከአለው ከደሙ ወስዶ በአሮንና በልብሱ ላይ ፥ በልጆቹና በልጆቹ ልብስ ላይ ረጨው፤ አሮንንና ልብሱንም፥ ልጆቹንም፥ የልጆቹንም ልብስ ቀደሰ።
ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ በኀይልም እንደ ቀባው፥ እየዞረም መልካም እንደ አደረገ፥ ሰይጣን ያሸነፋቸውንም እንደ ፈወሰ ታውቃላችሁ። እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና።