ሕዝቅያስም የካህናትንና የሌዋውያንን ሰሞን በየክፍላቸውና በየአገልግሎታቸው፥ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ በሮች የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቀርቡና ያገለግሉ ዘንድ፥ ያመሰግኑም፥ ያከብሩም ዘንድ ካህናቱንና ሌዋውያኑን መደበ።
ዘሌዋውያን 19:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የድኅነትን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ስትሠዉ ንጹሕ አድርጋችሁ ሠዉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘የኅብረት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በምታቀርቡበት ጊዜ፣ መሥዋዕታችሁ ተቀባይነት እንዲያገኝላችሁ አድርጋችሁ አቅርቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የአንድነትንም መሥዋዕት ለጌታ ስትሰዉ እንዲሠምርላችሁ አድርጋችሁ ሠዉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለአንድነት መሥዋዕት አንድ ዐይነት እንስሳ በምተሠዉበት ጊዜ፥ የሰጠኋችሁን ሥርዓት ጠብቁ፤ መሥዋዕቱም በእኔ ዘንድ ተቀባይነት ይኖረዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የደኅንነትንም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ስትሰዉ እርሱን ደስ እንድታሰኙበት ሠውት። |
ሕዝቅያስም የካህናትንና የሌዋውያንን ሰሞን በየክፍላቸውና በየአገልግሎታቸው፥ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ በሮች የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቀርቡና ያገለግሉ ዘንድ፥ ያመሰግኑም፥ ያከብሩም ዘንድ ካህናቱንና ሌዋውያኑን መደበ።
የእስራኤልንም ልጆች ጐልማሶች ላከ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትንም አቀረቡ፤ ለእግዚአብሔርም ስለ ደኅንነት መሥዋዕት በሬዎችን ሠዉ።
አለቃውም በፈቃዱ የሚያቀርበውን መሥዋዕት፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ወይም በፈቃዱ ለእግዚአብሔር የሚያቀርበውን የደኅንነቱን መሥዋዕት በአቀረበ ጊዜ፥ ወደ ምሥራቅ የሚመለከተው በር ይከፈትለት፤ በሰንበትም ቀን እንደሚያደርግ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቅርብ፤ ከዚያም በኋላ ይውጣ፤ ከወጣም በኋላ በሩ ይዘጋ።
አለቃው በስተ ውጭ ባለው በር በደጀ ሰላሙ መንገድ ገብቶ በበሩ መቃን አጠገብ ይቁም፤ ካህናቱም የእርሱን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቅርቡ፥ እርሱም በበሩ መድረክ ላይ ይስገድ፤ ከዚያም በኋላ ይውጣ፤ በሩ ግን እስከ ማታ ድረስ አይዘጋ።
“መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከላሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እንዲኖረው በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል።
ጣዖታትንም አትከተሉ፤ ቀልጠው የተሠሩትንም የአማልክት ምስሎች ለእናንተ አታድርጉ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
ማናቸውም ሰው ስእለቱን ለመፈጸም ወይም በፈቃዱ ለማቅረብ የደኅንነትን መሥዋዕት፥ ወይም በሬን፥ ወይም በግን፥ ለእግዚአብሔር ቢያቀርብ፥ ይሰምርለት ዘንድ ፍጹም ይሁን፤ ነውርም አይሁንበት።
በሬው፥ ወይም በጉ ጆሮው፥ ወይም ጅራቱ የተቈረጠ ቢሆን፥ ቈጥረህ የራስህ ገንዘብ አድርገው እንጂ ለስእለት አይቀበልህም።
የቍርባኑም መሥዋዕት የስእለት ወይም የፈቃድ ቢሆን፥ መሥዋዕቱ በሚቀርብበት ቀን ይብሉት፤ ከእርሱም የቀረውን በነጋው ይብሉት፤
በሦስተኛው ቀን ከደኅንነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፥ አይሠምርም፤ ላቀረበው ሰው የተጠላ ይሆንበታል እንጂ ቍርባን ሆኖ አይቈጠርለትም፤ ከእርሱም የበላ ሰው ኀጢአቱን ይሸከማል።