ዘሌዋውያን 14:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኀጢአትን መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያርዱበት በተቀደሰው ስፍራ ጠቦቱን ያርዱታል፤ የበደሉ መሥዋዕት ለካህኑ እንደሚሆን፥ እንዲሁ የኀጢአቱ መሥዋዕት ነውና፤ ቅዱሰ ቅዱሳን ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠቦቱንም፣ የኀጢአት መሥዋዕትና የሚቃጠል መሥዋዕት በሚታረድበት በተቀደሰው ስፍራ ይረደው፤ የኀጢአት መሥዋዕቱ ለካህኑ እንደሚሰጥ ሁሉ የበደል መሥዋዕቱም ለካህኑ ይሰጥ፤ ይህም እጅግ የተቀደሰ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኃጢአትን መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያርድበት በተቀደሰው ስፍራ ጠቦቱን ያርደዋል፤ እንደ ኃጢአት መሥዋዕቱም እንዲሁ የበደል መሥዋዕቱ ለካህኑ ይሆናል፤ እርሱም እጅግ የተቀደሰ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠቦቱንም ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕትና ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶች በሚታረዱበት ቅዱስ ስፍራ ያርደዋል፤ ይህንንም የሚያደርግበት ምክንያት የበደል ዕዳ መሥዋዕት ልክ ለኃጢአት ስርየት እንደሚቀርበው መሥዋዕት የካህኑ ድርሻ ሆኖ ስለሚሰጥ ነው፤ እርሱም እጅግ የተቀደሰ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኃጢአትን መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያርዱበት በተቀደሰው ስፍራ ጠቦቱን ያርደዋል፤ የኃጢአቱ መሥዋዕት ለካህኑ እንደሚሆን፥ እንዲሁ የበደል መሥዋዕት ነው፤ ቅዱሰ ቅዱሳን ነው። |
እንዲህም አለኝ፥ “በልዩ ስፍራ አንጻር በሰሜንና በደቡብ በኩል ያሉ ዕቃ ቤቶች፥ እነርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡ የሳዶቅ ልጆች ካህናቱ ከሁሉ ይልቅ የተቀደሰውን ምግብ የሚበሉባቸው ቤቶች ናቸው። ስፍራው ቅዱስ ነውና በዚያ የተቀደሰውን ነገር፥ የእህሉን ቍርባን፥ የኀጢአቱንና የበደሉን መሥዋዕት ያኖራሉ።
በመሠዊያውም አጠገብ በመስዕ በኩል በእግዚአብሔር ፊት ያርዱታል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።
በሬውንም በእግዚአብሔር ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን ያቀርባሉ፤ ደሙንም በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ፊት ባለው በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።
“ቅዱሰ ቅዱሳን ነውና፥ የሕዝቡንም ኀጢአት እንድትሸከሙ፥ በእግዚአብሔርም ፊት እንድታስተሰርዩላቸው ይህን ትበሉ ዘንድ ለእናንተ ሰጥቶታልና ስለ ምን የኀጢአትን መሥዋዕት በቅዱሱ ስፍራ አልበላችሁም?
በፍየሉም ራስ ላይ እጁን ይጭናል፤ የሚቃጠልም መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ በእግዚአብሔር ፊት ያርደዋል፤ እርሱ የኀጢአት መሥዋዕት ነውና።
ወይፈኑንም ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ በእግዚአብሔር ፊት ያመጣዋል፤ እጁንም በወይፈኑ ራስ ላይ ይጭነዋል፤ ወይፈኑንም በእግዚአብሔር ፊት ያርደዋል።
የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያርዱበት ስፍራ የበደሉን መሥዋዕት በግ በዚያ ያርዱታል፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል።