ዘሌዋውያን 13:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የለምጽ ደዌ ያለበት ሰው ልብሱ የተቀደደ ይሁን፤ ራሱም የተገለጠ ይሁን፤ ከንፈሩንም ይሸፍን፤ ርኩስ ይባላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንዲህ ያለ ተላላፊ በሽታ ያለበት ሰው የተቀደደ ልብስ ይልበስ፤ ጠጕሩን ይግለጥ፤ እስከ አፍንጫውም ድረስ ተሸፋፍኖ ‘ርኩስ ነኝ! ርኩስ ነኝ!’ እያለ ይጩኽ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የለምጽ ደዌ ያለበት ሰው የሚለብሳቸው ልብሶች የተቀደዱ ይሁኑ፥ የራሱም ጠጉር የተጐሳቈለ ይሁን፥ ከንፈሩንም ይሸፍን፤ ርኩስ ርኩስ ነኝ እያለ ይጩኽ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በዚህ ዐይነት የሥጋ ደዌ በሽታ ያለበት ሰው የተቀዳደደ ልብስ ይልበስ፤ ጠጒሩን አያበጥር፥ ከንፈሩን ይሸፍን፤ ከዚያም በኋላ ‘እኔ የረከስኩ ነኝ! የረከስኩ ነኝ!’ እያለ ይጩኽ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የለምጽ ደዌ ያለበት ሰው ልብሱ የተቀደደ ይሁን፥ ራሱም የተገለጠ ይሁን፥ ከንፈሩንም ይሸፍን፤ ርኩስ ርኩስ ነኝ ይበል። |
ትዕማርም አመድ ወስዳ በራስዋ ላይ ነሰነሰች፤ በላይዋ የነበረውንም ብዙ ኅብር ያለውን ልብስዋን ቀደደችው፤ እጅዋንም በራስዋ ላይ ጭና እየጮኸች ሄደች።
ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያፈርስሃል፤ ከቤትህም ይነቅልሃል፥ ያፈልስሃልም፥ ሥርህንም ከሕያዋን ምድር።
እናንተ የእግዚአብሔርን ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፤ እልፍ በሉ፤ ከዚያ ውጡ፤ ርኩስን ነገር አትንኩ፤ ከመካከልዋ ውጡ፤ ራሳችሁን ለዩ።
እኔም፥ “ከንፈሮች የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸው በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዐይኖች የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ!” አልሁ።
ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፤ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ በኀጢአታችን ምክንያት እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ እንዲሁም ነፋስ ጠራርጎ ወስዶናል።
ከትንሽነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባቶቻችን በአምላካችን በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ሠርተናልና፥ የአምላካችንንም የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማንምና በእፍረታችን ተኝተናል፤ ውርደታችንም ሸፍኖናል።”
ሳምኬት። እናንተ ከርኩሳን ራቁ፥ አስተምሩአቸው፤ ራቁ፥ ራቁ በሉአቸው፤ አትንኩአቸውም። ታውከዋልና ዳግመኛ እንዳይኖሩባት ለአሕዛብ ንገሩአቸው።
በቀስታ ተክዝ፤ ነገር ግን የሙታንን ልቅሶ አታልቅስ፤ መጠምጠሚያህን በራስህ ላይ አድርግ፤ ጫማህንም በእግርህ አጥልቅ፤ ከንፈሮችህንም አትሸፍን፤ የዕዝን እንጀራንም አትብላ።”
ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ፥ ቍጣው የዘገየ ምሕረቱም የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ።”
ሙሴም አሮንን፥ ልጆቹንም አልዓዛርንና ኢታምርን፥ “እንዳትሞቱ፥ በማኅበሩም ላይ ሁሉ ቍጣ እንዳይወርድ ራሳችሁን አትንጩ፤ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፤ እግዚአብሔር ስላቃጠላቸው ማቃጠል ግን ወንድሞቻችሁ የእስራኤል ቤት ሁሉ ያልቅሱ።
“በራሱም ላይ የቅባት ዘይት የፈሰሰበት፥ የክህነትም ልብስ ይለብስ ዘንድ የተቀደሰ፥ ከወንድሞቹ የተለየው ካህን ራሱን አይላጭ፤ ልብሱንም አይቅደድ።
“የእስራኤል ልጆች ለምጻሙን ሁሉ ፈሳሽ ነገርም ያለበትን ሁሉ በሰውነቱ የረከሰውን ሁሉ ከሰፈሩ እንዲያወጡ እዘዛቸው፤
ስምዖን ጴጥሮስም ይህን አይቶ ከጌታችን ከኢየሱስ እግር በታች ሰገደና፥ “እኔ ኀጢአተኛ ሰው ነኝና አቤቱ ከእኔ ፈቀቅ በል፤” አለው።