በኢዮአብ ራስ ላይና በአባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይምጣበት፤ በኢዮአብም ቤት ፈሳሽ ነገር ያለበት ወይም ለምጻም ወይም አንካሳ ወይም በሰይፍ የሚወድቅ ወይም እንጀራ የሌለው ሰው አይታጣ።”
ዘሌዋውያን 13:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሰው በሥጋው ቆዳ ላይ እባጭ ብትወጣበት፥ ብትነጣም፥ በሥጋውም ቆዳ እንደ ለምጽ ደዌ ብትመስል፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ከካህናቱ ልጆች ወደ አንዱ ያምጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ማንኛውም ሰው በሰውነቱ ቈዳ ላይ ዕብጠት ወይም ችፍታ ወይም ቋቍቻ ቢወጣበትና ይህም ወደ ተላላፊ የቈዳ በሽታ የሚለወጥበት ከሆነ፣ ወደ ካህኑ አሮን ወይም ካህናት ከሆኑት ልጆቹ ወደ አንዱ ያምጡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማናቸውም ሰው በሰውነቱ ቆዳ ላይ እባጭ ወይም ብጉር ወይም ቋቁቻ ቢታይ፥ በሰውነቱ ቆዳ እንደ ለምጽ ደዌ ቢሆን፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ካህናት ከሆኑት ከልጆቹ ወደ አንዱ ያምጡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ማንም ሰው በሰውነቱ ላይ እባጭ ወይም ሽፍታ ወይም ቋቊቻ ቢታይና በገላው ላይ የሥጋ ደዌ ቢመስል፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ካህናት ከሆኑት ከልጆቹ ወደ አንዱ ያምጡት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማናቸውም ሰው በሥጋው ቁርበት ላይ እባጭ ወይም ብጉር ወይም ቍቁቻ ቢታይ፥ በሥጋው ቁርበት እንደ ለምጽ ደዌ ቢመስል፥ ወደ ካህኑ ወደ አሮን ወይም ከካህናቱ ልጆቹ ወደ አንዱ ያምጡት። |
በኢዮአብ ራስ ላይና በአባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይምጣበት፤ በኢዮአብም ቤት ፈሳሽ ነገር ያለበት ወይም ለምጻም ወይም አንካሳ ወይም በሰይፍ የሚወድቅ ወይም እንጀራ የሌለው ሰው አይታጣ።”
የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ ንዕማንም እግዚአብሔር በእርሱ እጅ ለሶርያ ደኅንነትን ስለ ሰጠ፥ በጌታው ዘንድ ታላቅና ክቡር ሰው ነበረ፤ ሰውዬውም ጽኑዕ፥ ኀያል ነበረ፤ ነገር ግን ለምጻም ነበረ።
ነገር ግን የንዕማን ለምጽ በአንተና በዘርህ ላይ፥ ለዘለዓለም ይመለስ” አለው። እንደ በረዶም ለምጻም ሆኖ ከእርሱ ዘንድ ወጣ።
ከእግር ጫማ አንሥቶ እስከ ራስ ድረስ ጤና የለውም፤ ቍስልና እበጥ የሚመግልም ነው፤ አልፈረጠም፤ አልተጠገነምም፤ በዘይትም አልለዘበም።
ካህኑም በሥጋው ቆዳ ያለችውን ያችን ደዌ ይያት፤ ጠጕሯም ተለውጣ ብትነጣ በሥጋው ቆዳ ያለች የዚያች ደዌ መልክ ቢከፋ፥ ደዌውም ወደ ሥጋው ቆዳ ቢጠልቅ፥ እርስዋ የለምጽ ደዌ ናት፤ ካህኑም አይቶ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይበለው።
ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነውና ከንፈሮቹ እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ይገባቸዋል፥ ሰዎችም ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል።
ደመናውም ከድንኳኑ ተነሣ፤ እነሆም፥ ማርያም ለምጻም ሆነች፤ እንደ በረዶም ነጭ ሆነች፤ አሮንም ማርያምን ተመለከተ፤ እነሆም፥ ለምጻም ሆና ነበር።
ኢየሱስም “ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ሙሴ ያዘዘውን መባ አቅርብ” አለው።
“ለማንም አንዳች እንዳትናገር ተጠንቀቅ፤ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፤ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለ መንጻትህ ሙሴ ያዘዘውን አቅርብ፤” አለው።
ለማንም እንዳይናገር ከለከለው፤ “ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አስመርምር፤ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ ነጻህ ሙሴ እንደ አዘዘ መባህን አቅርብ” ብሎ አዘዘው።
“ስለ ለምጽ ደዌ ሌዋውያን ካህናት ያስተማሩህን ሁሉ ፈጽመህ እንድትጠብቅ እንድታደርግም ተጠንቀቅ፤ እኔ ያዘዝኋቸውን እንዲሁ ታደርግ ዘንድ ጠብቅ።