ሰቈቃወ 5:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን፤ እኛም እንመለሳለን፤ ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ መልሰን፤ እኛም እንመለሳለን፤ ዘመናችንን እንደ ቀድሞው አድስ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፥ ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! እንደገና እንቋቋም ዘንድ ወደ አንተ መልሰን! ሁኔታችንን አድሰህ እንደ ቀድሞ ዘመን አድርገው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፥ ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ። |
እግዚአብሔር የዘለዓለም ብርሃንሽ ይሆናልና፥ የልቅሶሽም ወራት ያልፋልና፤ ፀሐይሽ ከዚህ በኋላ አትጠልቅም፤ ጨረቃሽም አይቋረጥም።
ልጆቻቸውም እንደ ቀድሞው ይሆናሉ፤ ምስክርነታቸውም በፊቴ ጸንቶ ይኖራል፤ የሚያስጨንቁአቸውንም ሁሉ እቀጣለሁ።
“ኤፍሬም ሲጨነቅ መስማትን ሰማሁ፤ እንዲህም አለ፦ ቀጣኸኝ እኔም እንዳልቀና ወይፈን ተቀጣሁ፤ አንተ እግዚአብሔር አምላኬ ነህና መልሰኝ፤ እኔም እመለሳለሁ።
የእስራኤል ድንግል ሆይ እንደ ገና እሠራሻለሁ፤ አንቺም ትሠሪያለሽ፤ እንደ ገናም ከበሮሽን አንሥተሽ ከዘፋኞች ጋር ትወጫለሽ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እናንተ፦ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ያለች ባድማ ናት በምትሉአት በዚች ስፍራ፥ የሚቀመጥባቸው በሌለ፥ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ባድማ በሆኑ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ፥
በደጋው ላይ ባሉ ከተሞች፥ በቆላውም ባሉ ከተሞች፥ በደቡብም ባሉ ከተሞች፥ በብንያምም ሀገር፥ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች በጎቹ በተቈጣጣሪያቸው እጅ እንደ ገና ያልፋሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።”
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለዚህ ደግሞ አደርግላቸው ዘንድ የእስራኤል ቤት ይሹኛል፤ ሰውንም እንደ መንጋ አበዛላቸዋለሁ።