ሰቈቃወ 3:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጸሎታችን እንዳያርግ ራስህን በደመና ከደንህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጸሎት እንዳያልፍ፣ ራስህን በደመና ሸፈንህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጸሎት እንዳያልፍ ራስህን በደመና ከደንህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጸሎት አልፎ ሊገባ በማይችልበት ራስህን ጥቅጥቅ ባለ ደመና ሸፈንክ። መኖሪያህን በደመና ሸፈንክ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጸሎት እንዳያልፍ ራስህን በደመና ከደንህ። |
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አያዘነብልም፤ እነዚህን ሕዝቦች ከፊቴ አባርራቸው፤ ይውጡ።
አሌፍ። እግዚአብሔር በቍጣው መቅሠፍት የጽዮንን ሴት ልጅ ምንኛ አጠቈራት! የእስራኤልን ክብር ከሰማይ ወደ ምድር ጣለ፤ በቍጣውም ቀን የእግሩን መረገጫ አላሰበም።