በዚያም ዘመን ለሚወጣውና ለሚገባው ሰላም አይሆንለትም፤ በሀገሮችም በሚኖሩት ሁሉ ላይ ታላቅ የእግዚአብሔር ቍጣ ይሆናል።
መሳፍንት 5:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሐናት ልጅ በሰሜጋር ዘመን፥ በኢያዔል ዘመን ነገሥት መንገዶችን ተዉ፤ በስርጥ መንገድም ይሄዱ ነበር፤ በጠማማ መንገድም ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዓናት ልጅ በሰሜጋር ዘመን፣ በኢያዔል ጊዜ መንገዶች ባድማ ሆኑ፤ ተጓዦችም በጠመዝማዛ መንገድ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዓናት ልጅ በሻምጋር ዘመን፥ በያዔል ዘመን መንገዶች ተቋረጡ፥ መንገደኞች በስርጥ መንገድ ይሄዱ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዐናት ልጅ በሻምጋርና በያዔል ዘመን፥ የሲራራ ነጋዴዎች በምድሪቱ አያልፉም ነበር፤ መንገደኞችም ተደብቀው በዘወርዋራ መንገድ ይሄዱ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዓናት ልጅ በሰሜጋር ዘመን፥ በኢያዔል ዘመን መንገዶች ተቋረጡ፥ መንገደኞች በስርጥ መንገድ ይሄዱ ነበር። |
በዚያም ዘመን ለሚወጣውና ለሚገባው ሰላም አይሆንለትም፤ በሀገሮችም በሚኖሩት ሁሉ ላይ ታላቅ የእግዚአብሔር ቍጣ ይሆናል።
ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓል የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች አለቀሱ፤ በሮችዋ ሁሉ ፈርሰዋል፤ ካህናቷም ያለቅሳሉ፤ ደናግሎችዋም ተማረኩ፤ እርስዋም በምሬት አለች።
ጻዴ። ልጆቻችንን ወደ አደባባያችን እንዳይወጡ ከለከልን፤ የምንጠፋበት ጊዜ ደርሷልና ዘመናችን አለቀ፤ የምንጠፋበትም ጊዜ ቀረበ።
በእናንተ ላይ ክፉዎች የምድርን አራዊት እሰድዳለሁ፤ ይበሉአችኋል፤ እንስሶቻችሁንም ያጠፋሉ፤ እናንተንም ያሳንሳሉ፤ መንገዶቻችሁም በረሃ ይሆናሉ።
ከእርሱም በኋላ የሐናት ልጅ ሴሜጋር ተነሣ፤ ከፍልስጥኤማውያንም ስድስት መቶ ሰው በበሬ መውጊያ ገደለ፤ እርሱም ደግሞ እስራኤልን አዳነ።