እነርሱ ግን እንዲህ አሉ፥ “የወይኑን ጠጅ አንጠጣም፤ አባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ እናንተና ልጆቻችሁ ለዘለዓለም የወይን ጠጅ አትጠጡ ብሎ አዝዞናልና።
መሳፍንት 13:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከወይንም ከሚወጣው ሁሉ አትብላ፤ የወይን ጠጅንና የሚያሰክር መጠጥንም አትጠጣ፤ ርኩስንም ነገር ሁሉ አትብላ፤ ያዘዝኋትን ሁሉ ጠብቁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከወይን ተክል የሚገኝ ማንኛውንም ነገር አትብላ፤ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጣ፤ ርኩስ ነገር አትብላ፤ ያዘዝኋትንም ሁሉ ታድርግ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከወይን ተክል የሚገኝ ማንኛውንም ነገር አትብላ፤ የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጣ፤ ርኩስ ነገር አትብላ፤ እኔ ያዘዝኳትን ሁሉ ታድርግ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከወይን ተክል የሚገኝ ምንም ነገር መመገብ አይኖርባትም፤ የወይን ጠጅም ሆነ ማንኛውንም የሚያሰክር መጠጥ አትጠጣ፤ ማንኛውንም ርኩስ ምግብ አትበላም፤ በአጠቃላይ እኔ ያዘዝኳትን ሁሉ መፈጸም አለባት።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከወይንም ከሚወጣው ሁሉ አትብላ፥ የወይን ጠጅንም የሚያሰክርንም ነገር አትጠጣ፥ ርኩስም ነገር ሁሉ አትብላ፥ ያዘዝኋትን ሁሉ ትጠብቅ አለው። |
እነርሱ ግን እንዲህ አሉ፥ “የወይኑን ጠጅ አንጠጣም፤ አባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ እናንተና ልጆቻችሁ ለዘለዓለም የወይን ጠጅ አትጠጡ ብሎ አዝዞናልና።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ወንድ ወይም ሴት ለእግዚአብሔር ራሱን የተለየ ያደርግ ዘንድ ልዩ ስእለት ቢሳል፥
እርሱም፦ እነሆ፥ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ እንግዲህ የወይን ጠጅንና የሚያሰክር መጠጥን አትጠጪ፥ ርኩስ ነገርንም አትብዪ፤ ልጁ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ እስኪሞት ድረስ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና አለኝ” ብላ ተናገረች።