ያንጊዜም ሰሎሞን ለሞአብ ርኵሰት ለኮሞስ፥ ለአሞን ልጆች ርኵሰት ለሞሎክ በኢየሩሳሌም አንጻር በአለው ተራራ ላይ መስገጃን ሠራ።
መሳፍንት 11:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህ ኮሞስ የሚሰጥህን የምትወርስ አይደለህምን? እኛም አምላካችን እግዚአብሔር ከፊታችን ያስወጣቸውን የእነርሱን ምድር የምንወርስ አይደለንምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ ካሞሽ የሰጠህን ይዞ ማቈየቱ ያንተ ፈንታ ነው፤ እኛም እንደዚሁ አምላካችን እግዚአብሔር የሰጠንን ሁሉ ርስት አድርገን እንወርሳለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላክህ ካሞሽ የሰጠህን ይዞ ማቈየቱ ያንተ ፈንታ አይደለምን? እኛስ እንደዚሁ አምላካችን ጌታ የሰጠንን ሁሉ ርስት አድርገን ልንወርስ አይገባንምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ አምላክህ ከሞሽ የሰጠህን ይዘህ ዐርፈህ አትቀመጥምን? እኛ ግን አምላካችን እግዚአብሔር የሰጠንን ሁሉ ወርሰን እንኖራለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ ካሞሽ የሚሰጥህን አትወርስምን? እኛም አምላካችን እግዚአብሔር ከፊታችን ያስወጣቸውን የእነርሱን ምድር እንወርሳለን። |
ያንጊዜም ሰሎሞን ለሞአብ ርኵሰት ለኮሞስ፥ ለአሞን ልጆች ርኵሰት ለሞሎክ በኢየሩሳሌም አንጻር በአለው ተራራ ላይ መስገጃን ሠራ።
ሞአብ ሆይ! ወዮልሽ! የካሞሸ ወገን ጠፍቶአል፤ ወንዶች ልጆችሽ ተማርከው ተወስደዋልና፥ ሴቶች ልጆችሽም ወደ ምርኮ ሄደዋልና።
በሥራሽና በመዝገብሽ ታምነሻልና አንቺ ደግሞ ትያዢያለሽ፤ ካሞሽም ከካህናቱና ከአለቆቹ ጋር በአንድነት ይማረካል።
ሞዓብ ሆይ፥ ወዮልህ! የካሞስ ሕዝብ ሆይ፥ ጠፋህ፤ ወንዶች ልጆቻቸውን ለማደን፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለምርኮ፤ ለአሞራውያን ንጉሥ ለሴዎን ሰጠ።
ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው፤ ስለዚህም ርኵሰት አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ ያጠፋቸዋል።
እግዚአብሔርም ይሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም።
ኢያሱም አለ፥ “ሕያው አምላክ በመካከላችሁ እንደ ሆነ፥ እርሱም ከፊታችሁ ከነዓናዊውን፥ ኬጤዎናዊውንም፥ ኤዌዎናዊውንም፥ ፌርዜዎናዊውንም፥ ጌርጌሴዎናዊውንም፥ አሞሬዎናዊውንም፥ ኢያቡሴዎናዊውንም ፈጽሞ እንዲያጠፋቸው በዚህ ታውቃላችሁ።
የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ በዓሊምንና አስታሮትን፥ የሶርያንም አማልክት፥ የሲዶናንም አማልክት፥ የሞዓብንም አማልክት፥ የአሞንንም ልጆች አማልክት፥ የፍልስጥኤማውያንንም አማልክት አመለኩ፤ እግዚአብሔርንም ተዉ፤ አላመለኩትምም።
አሁንም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ከእስራኤል ፊት አሞሬዎናውያንን አስወገደ፤ አንተም በተራህ ትወርሳለህን?
የእግዚአብሔርም መልአክ ከገልገላ ወደ ቀላውትምኖስ ወደ ቤቴል ወደ እስራኤል ቤት ወጥቶ እንዲህ አላቸው፥ “እግዚአብሔር እኔ ከግብፅ አውጥቼአችኋለሁ፤ እሰጣችሁም ዘንድ ለአባቶቻችሁ ወደ ማልሁላቸው ምድር አግብቻችኋለሁ፤ እኔም፦ ከእናንተ ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን ለዘለዓለም አላፈርስም፤