ለዳዊትም ስለ ሰዎቹ ነገሩት፤ ሰዎቹ እጅግ አፍረው ነበሩና ተቀባዮችን ላከ። ንጉሡም፥ “ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያሪኮ ተቀመጡ፤ ከዚያም በኋላ ተመለሱ” አላቸው።
ኢያሱ 6:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከተማዪቱንም፥ በእርስዋም የነበረውን ሁሉ በእሳት አቃጠሉ፤ ነገር ግን ብሩንና ወርቁን፥ የናሱንና የብረቱንም ዕቃ በእግዚአብሔር ግምጃ ቤት ውስጥ አገቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ከተማዪቱን በሙሉ፣ በውስጧ ያለውንም ሁሉ አቃጠሉ፤ ብሩንና ወርቁን፣ የናሱንና የብረቱን ዕቃ ግን በእግዚአብሔር ግምጃ ቤት አኖሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተማይቱንም በእርሷም የነበረውን ሁሉ በእሳት አቃጠሉ፤ ነገር ግን ብሩንና ወርቁን የናሱንና የብረቱንም ዕቃ ብቻ በጌታ ግምጃ ቤት አኖሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ በእግዚአብሔር ዕቃ ግምጃ ቤት ካስቀመጡአቸው ከብሩና ከወርቁ እንዲሁም በነሐስና በብረት ከተሠሩት ዕቃዎች በቀር ከተማይቱንና በእርስዋ ያሉትን ነገሮች ሁሉ አቃጠሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከተማይቱንም በእርስዋም የነበረውን ሁሉ በእሳት አቃጠሉ፥ ነገር ግን ብሩንና ወርቁን የናሱንና የብረቱንም ዕቃ በእግዚአብሔር ግምጃ ቤት አደረጉት። |
ለዳዊትም ስለ ሰዎቹ ነገሩት፤ ሰዎቹ እጅግ አፍረው ነበሩና ተቀባዮችን ላከ። ንጉሡም፥ “ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያሪኮ ተቀመጡ፤ ከዚያም በኋላ ተመለሱ” አላቸው።
የንጉሡም የአበዛዎች አለቃ የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት አቃጠለ። የኢየሩሳሌምንም ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ።
ንጉሡም ዳዊት ከአሕዛብ ሁሉ ከኤዶምና ከሞዓብ፥ ከአሞንም ልጆች፥ ከፍልስጥኤማውያንም፥ ከአማሌቅም ከማረከው ብርና ወርቅ ጋር እነዚህን ደግሞ ለእግዚአብሔር ቀደሰ።
ዕቃዋንም ሁሉ ወደ አደባባይዋ ትሰበስባለህ፤ ከተማይቱንም፥ ዕቃዋንም ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት በእሳት ፈጽመህ ታቃጥላለህ፤ ለዘለዓለምም ወና ትሆናለች፤ ደግሞም አትሠራም።
የእግዚአብሔር የመቅሠፍቱ ቍጣ ይመለስ ዘንድ፥ ለአባቶችህም እንደ ማለላቸው ይምርህ ዘንድ፥ ይራራልህም ዘንድ፥ ያበዛህም ዘንድ፥ ርጉም ከሆነው አንዳች ነገር በእጅህ አትንካ።
በእርስዋም ያሉትን ሰዎች ሁሉ በሰይፍ ገደሉ፤ እስትንፋስ ያላቸውንም ሁሉ ሳያስቀሩ ሁሉንም አጠፉአቸው፤ አሶርንም በእሳት አቃጠላት፤
ነገር ግን ብርና ወርቅ ሁሉ፥ የናስና የብረትም ዕቃ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሁን፤ ወደ እግዚአብሔርም ግምጃ ቤት ይግባ።”
ኢያሪኮን ሊሰልሉ ኢያሱ የላካቸውንም መልእክተኞች ስለ ሸሸገች ዘማዊቱን ረዓብን፥ የአባቷንም ቤተ ሰብ፥ ያላትንም ሁሉ ኢያሱ አዳናቸው፤ እርስዋም በእስራኤል መካከል እስከ ዛሬ ድረስ ተቀምጣለች።
ኢያሱም ከተማዋን በእሳት አቃጠላት፤ ዐመድም ሆነች፤ እስከ ዛሬም ድረስ ለዘለዓለሙ የሚኖርባት እንዳይኖር አደረጋት።