በዲቦን የምትኖሪ ሆይ! ሞአብን የሚያጠፋ ወጥቶብሻልና፥ አምባሽንም ሰብሮአልና ከክብርሽ ውረጂ፤ በጭቃም ላይ ተቀመጪ።
ኢያሱ 6:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም ከተማዋን፥ በከተማዪቱም ውስጥ የነበሩትን ሁሉ፥ ከወንድ እስከ ሴት፥ ከሕፃን እስከ ሽማግሌ፥ ከበሬ እስከ በግና እስከ አህያ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በከተማዪቱ ውስጥ ያለውን ሁሉ፣ ማለትም ወንዱንና ሴቱን፣ ወጣቱንና ሽማግሌውን፣ ከብቱንና በጉን እንዲሁም አህያውን በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በከተማይቱም የነበሩትን ሁሉ፥ ወንዱንና ሴቱን፥ ሕፃኑንና ሽማግሌውን፥ በሬውንም በጉንም አህያውንም፥ በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰይፋቸውንም መዘው በከተማይቱ የተገኘውን ወንዱንም ሴቱንም ወጣቱንና ሽማግሌውን ሁሉ ገደሉ፤ የከብት፥ የበግና የአህያውን መንጋ ሁሉ ፈጁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በከተማይቱም የነበሩትን ሁሉ፥ ወንዱንና ሴቱን፥ ሕፃኑንና ሽማግሌውን፥ በሬውንም በጉንም አህያውንም፥ በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ። |
በዲቦን የምትኖሪ ሆይ! ሞአብን የሚያጠፋ ወጥቶብሻልና፥ አምባሽንም ሰብሮአልና ከክብርሽ ውረጂ፤ በጭቃም ላይ ተቀመጪ።
ዕቃዋንም ሁሉ ወደ አደባባይዋ ትሰበስባለህ፤ ከተማይቱንም፥ ዕቃዋንም ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት በእሳት ፈጽመህ ታቃጥላለህ፤ ለዘለዓለምም ወና ትሆናለች፤ ደግሞም አትሠራም።
በዚያን ጊዜም ከተሞቹን ሁሉ ወሰድን፤ ከተማውንም ሁሉ፥ ሴቶችንም፥ ሕፃኖችንም አጠፋን፤ አንዳችም የሸሸ በሕይወት አላስቀረንም፥
አምላክህም እግዚአብሔር የሚሰጥህን የአሕዛብ ምርኮ ትበላለህ፤ ዐይንህም አታዝንላቸውም፤ ያም ለአንተ ክፉ ይሆንብሃልና አማልክቶቻቸውን አታምልካቸው።
በዚያም ቀን መቄዳን ያዟት፤ እርስዋንና ንጉሥዋንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፤ በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽመው አጠፉአቸው፤ ከእነርሱም አንዱን ስንኳ አላስቀሩም፤ የዳነም፥ ያመለጠም የለም፤ በኢያሪኮም ንጉሥ እንዳደረጉ በመቄዳ ንጉሥ አደረጉ።
እርስዋንም፥ ንጉሥዋንም፥ ከተሞችዋንም ያዙ፤ በሰይፍም ስለት መቱአቸው፤ በእነርሱም ውስጥ ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽመው አጠፉ፤ ማንንም አላስቀረም፤ በኬብሮንና በንጉሥዋም እንዳደረገው እንዲሁ በዳቤርና በንጉሥዋ አደረገ።
በእርስዋም ያሉትን ሰዎች ሁሉ በሰይፍ ገደሉ፤ እስትንፋስ ያላቸውንም ሁሉ ሳያስቀሩ ሁሉንም አጠፉአቸው፤ አሶርንም በእሳት አቃጠላት፤
የእስራኤልም ልጆች የእነዚህን ከተሞች ምርኮ ሁሉ፥ ከብቶቹንም ለራሳቸው ዘረፉ፤ ሰዎቹን ሁሉ ግን እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍ ስለት መቱአቸው፤ እስትንፋስ ያለውንም ሁሉ አንድም አላስቀሩም።
በኢያሪኮና በንጉሥዋም እንዳደረግህ እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋ ታደርጋለህ፤ የከብቱን ምርኮ ግን ለራሳችሁ ትዘርፋላችሁ፤ ከከተማዪቱም በስተኋላ ይከብቧት ዘንድ ጦር ላክ” አለው።
እነዚያም ከከተማ ወጥተው ተቀበሉአቸው፤ በእስራኤል ልጆች ሠራዊት መካከልም አገቡአቸው፤ እኒያ ከወዲያ፥ እኒህም ከወዲህ ሆነው አንድ እንኳን ሳይቀርና ሳያመልጥ ገደሉአቸው።
አንድም ብርቱ መልአክ ትልቅን ወፍጮ የሚመስልን ድንጋይ አንሥቶ እንዲህ ሲል ወደ ባሕር ወረወረው “ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን እንዲህ ተገፍታ ትወድቃለች፤ ከእንግዲህም ወዲህ ከቶ አትገኝም።
አሁንም ሄደህ አማሌቅንና ኢያሬምን ምታ፤ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፤ ከእነርሱም የምታድነው የለም። አጥፋቸው፤ መከራም አጽናባቸው፤ የእነርሱ የሆነውን ሁሉ አጥፋ፤ ለያቸውም፤ አትማራቸውም፤ ወንዱንና ሴቱን፥ ብላቴናውንና ሕፃኑን፥ በሬውንና በጉን፥ ግመሉንና አህያውን ግደል።”