እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወጣ ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በእግዚአብሔር መልእክተኞች ይሳለቁ፥ ቃሉንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።
ኢያሱ 24:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም ሕዝቡን፥ “እርሱ ቅዱስ አምላክ ነውና፥ እርሱም ቀናተኛ አምላክ ነውና እግዚአብሔርን ማምለክ አትችሉም፤ ብታስቀኑት መተላለፋችሁንና ኀጢአታችሁን ይቅር አይልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱም ሕዝቡን እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔርን ማምለክ አትችሉም፤ እርሱ ቅዱስ አምላክና፤ ቀናተኛም አምላክ ነው፤ ዐመፃችሁን ወይም ኀጢአታችሁን ይቅር አይልም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “እርሱ ቅዱስ አምላክ ነውና፥ እርሱም ቀናተኛ አምላክ ነውና ጌታን ማገልገል አትችሉም፤ መተላለፋችሁንና ኃጢአታችሁን ይቅር አይልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ቅዱስና ቀናተኛ አምላክ ስለ ሆነ፥ እናንተ እርሱን ማገልገል አትችሉም፤ የምትሠሩትን ዐመፅና ኃጢአት ሁሉ ይቅር አይልም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም ሕዝቡን፦ እርሱ ቅዱስ አምላክ ነውና፥ እርሱም ቀናተኛ አምላክ ነውና እግዚአብሔርን ማምለክ አትችሉም፥ መተላለፋችሁንና ኃጢአታችሁን ይቅር አይልም። |
እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወጣ ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በእግዚአብሔር መልእክተኞች ይሳለቁ፥ ቃሉንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።
እግዚአብሔር እርሱ አምላካችን እንደ ሆነ ዕወቁ፤ እርሱ ፈጠረን፥ እኛም አይደለንም፤ እኛስ ሕዝቡ የመሰማርያውም በጎች ነን።
አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
ለብዙ ሺህ ጽድቅን የሚጠብቅ፥ ቸርነትን የሚያደርግ፥ አበሳንና መተላለፍን፥ ኀጢአትንም ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችንም ኀጢአት በልጆች፥ እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድም በልጅ ልጆች የሚያመጣ አምላክ ነው” ሲል አወጀ።
ዘግይቶ ይደርቃል፤ በውስጡም ልምላሜ ሁሉ አይገኝም፤ ከቲኣሳ የምትመጡ ሴቶች፥ ኑና ለሕዝቤ አልቅሱ፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና፤ ስለዚህ ፈጣሪው አይራራለትም፤ ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።
“ከዚህ መንገድ መልሱን፤ ከዚህም ፈቀቅ አድርጉን በሉ፤ የእስራኤልንም ቅዱስ ትምህርት ከእኛ ዘንድ አስወግዱ” ይሏቸዋል።
የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ “ብትጸጸትና ብታለቅስ ትድናለህ፤ የት እንዳለህም ታውቃለህ፤ በከንቱ ታምነሃልና፤ ኀይላችሁም ከንቱ ይሆናል፤ እናንተ ግን መስማትን እንቢ አላችሁ፤
ሙሴም አሮንን፥ “እግዚአብሔር፦ ወደ እኔ በሚቀርቡ እመሰገናለሁ፤ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ ብሎ የተናገረው ይህ ነው” አለው፤ አሮንም ደነገጠ።
እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና፤ ሰውነታችሁን ቀድሱ፤ ቅዱሳንም ሁኑ፤ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ቅዱስ ነኝና፤
በምድርም ላይ በሚሳብ ተንቀሳቃሽ ሁሉ ሰውነታችሁን አታሳድፉ። እኔ አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር ነኝ፤ እንግዲህ እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ።
እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው፣ እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው፣ እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል።
ዓይኖችህ ክፉ እንዳያዩ ንጹሐን ናቸው፥ ጠማምነትንም ትመለከት ዘንድ አትችልም፣ አታላዮችንስ ለምን ትመለከታለህ? ኃጢአተኛውስ ከእርሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሲውጠው ስለምን ዝም ትላለህ?
“ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።
እግዚአብሔር አሕዛብን ሁሉ፥ በምድሪቱም የተቀመጡትን አሞሬዎናውያንን ከፊታችን አሳደደ፤ ስለዚህ እርሱ አምላካችን ነውና እኛ እግዚአብሔርን እናመልካለን።”
እርሱም፥ “አሁን እንግዲህ በእናንተ ዘንድ ያሉትን ሌሎች አማልክት አርቁ፤ ልባችሁንም ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር አቅኑ” አላቸው።
የቤትሳሚስም ሰዎች፥ “በዚህ በቅዱሱ አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ማለፍ ማን ይችላል? የእግዚአብሔር ታቦት ከእኛ ወጥታ ወደ ማን ትሄዳለች?” አሉ።