ኢያሱ 19:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስድስተኛውም ዕጣ ለንፍታሌም ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስድስተኛው ዕጣ ለንፍታሌም ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስድስተኛውም ዕጣ ለንፍታሌም ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስድስተኛው ዕጣ ለንፍታሌም ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስድስተኛውም ዕጣ ለንፍታሌም ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ። |
ስለ ንፍታሌምም እንዲህ አለ፦ ንፍታሌም ከበጎ ነገር ጠግቦአል፤ የእግዚአብሔርንም በረከት ተሞልቶአል፤ ባሕርንና ሊባን ይወርሳል።
ድንበራቸውም ከመሐላም፥ ከሞላም፥ ከቤሴሜይን፥ ከአርሜ፥ ከናቦቅና፥ ከኢያፍታሜን እስከ ይዳም ድረስ ነበረ፤ መውጫውም በዮርዳኖስ ነበረ።
ንፍታሌምም የቤትሳሚስንና የቤቴኔስን ሰዎች አላጠፋቸውም፤ በምድሩም በተቀመጡት በከነዓናውያን መካከል ተቀመጡ፤ ነገር ግን በቤትሳሚስና በቤቴኔስ የሚኖሩ ሰዎች ገባሮች ሁኑላቸው።
ዲቦራም ልካ ከቃዴስ ንፍታሌም የአቢኒሔምን ልጅ ባርቅን ጠርታ እንዲህ አለችው፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ያዘዘህ አይደለምን? ሄደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤ ከአንተም ጋር ከንፍታሌምና ከዛብሎን ልጆች ዐሥር ሺህ ሰዎች ውሰድ፤