ከአልዓዛርና ከኢታምርም ልጆች መካከል የንዋያተ ቅዱሳቱና የእግዚአብሔር ቤት አለቆች ነበሩና እነዚህና እነዚያ እንዲህ በዕጣ ተመደቡ።
ኢያሱ 18:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም በእግዚአብሔር ፊት በሴሎ ዕጣ አጣጣላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱም በሴሎ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ ጣለላቸው፤ ምድሪቱንም እንደየነገዱ ደልድሎ ለእስራኤላውያን አከፋፈላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም በጌታ ፊት በሴሎ ዕጣ ጣለላቸው፤ በዚያም ኢያሱ ለእስራኤል ልጆች እንደየድርሻቸው ምድሩን ከፈለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱም እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ዕጣ አወጣላቸው፤ ለቀሩትም ለእስራኤል ነገዶች ለእያንዳንዳቸው ተመጣጣኝ የሆነ የርስት ድርሻ ተመደበላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም በእግዚአብሔር ፊት በሴሎ ዕጣ አጣጣላቸው፥ በዚያም ኢያሱ ለእስራኤል ልጆች እንደ ክፍሎቻቸው ምድሩን ከፈለ። |
ከአልዓዛርና ከኢታምርም ልጆች መካከል የንዋያተ ቅዱሳቱና የእግዚአብሔር ቤት አለቆች ነበሩና እነዚህና እነዚያ እንዲህ በዕጣ ተመደቡ።
የሕዝቡም አለቆች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፤ ከቀሩትም ሕዝብ ከዐሥሩ ክፍል አንዱ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፥ ዘጠኙም በሌሎች ከተሞች ይቀመጡ ዘንድ ዕጣ ተጣጣሉ።
“ነገር ግን በቀድሞ ዘመን ስሜን ወዳሳደርሁበት በሴሎ ወደ ነበረው ስፍራዬ ሂዱ፤ ከሕዝቤም ከእስራኤል ክፋት የተነሣ ያደረግሁበትን እዩ።
ለእናንተና በእናንተ መካከል ለሚቀመጡ፥ በእናንተም መካከል ልጆችን ለሚወልዱ መጻተኞች ርስት አድርጋችሁ በዕጣ ትካፈሉአታላችሁ፤ እነርሱም በእስራኤል ልጆች መካከል እንደ አሉ የሀገር ልጆች ይሆኑላችኋል፤ በእስራኤልም ነገዶች መካከል ከእናንተ ጋር ርስትን ይወርሳሉ።
ርስት አድርጋችሁ ለእስራኤል ነገዶች በዕጣ የምታካፍሉአት ምድር ይህች ናት፤ የእያንዳንዱም ዕጣ እንደዚህ ነው፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ይኸውም ዐይናቸውን ትከፍትላቸው ዘንድ፥ ከጨለማም ወደ ብርሃን፥ ሰይጣንን ከማምለክም ወደ እግዚአብሔር ትመልሳቸው ዘንድ፥ ኀጢአታቸውም ይሰረይላቸው ዘንድ፥ በስሜም በማመን ከቅዱሳን ጋር አንድነትን ያገኙ ዘንድ ነው።’
የብንያምም ነገድ ዕጣ በየወገኖቻቸው በቅድሚያ ወጣ፤ የዕጣቸውም ዳርቻ በይሁዳ ልጆችና በዮሴፍ ልጆች መካከል ወጣ።
እናንተም ምድሪቱን በሰባት ክፍል ክፈሏት፤ ወደ እኔም ወዲህ አምጡልኝ፤ በአምላካችንም በእግዚአብሔር ፊት በዚህ ዕጣ አጣጥላችኋለሁ።
ሰዎችም ተነሥተው ሄዱ፤ ኢያሱም ምድሩን ሊጽፉ የሄዱትን፥ “ሂዱ፤ ምድሩንም ዞራችሁ ጻፉት፤ ወደ እኔም ተመለሱ፤ በዚህም በሴሎ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ አጣጥላችኋለሁ” ብሎ አዘዛቸው።
ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ የእስራኤልም ልጆች ነገዶች የአባቶች አለቆች በእግዚአብሔር ፊት በሴሎ በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በዕጣ የተካፈሉት ርስት ይህ ነው። ምድሪቱንም መካፈል ፈጸሙ።
እነሆ እኔ ካጠፋኋቸው አሕዛብ ሁሉ ጋር ከዮርዳኖስ ጀምሮ በፀሐይ መግቢያ እስካለው እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ለነገዶቻችሁ ርስት እንዲሆኑ የቀሩትን እነዚህን አሕዛብ በዕጣ ከፈልሁላችሁ።