ከዚህም በኋላ በጋዜር ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት እንደ ገና ሆነ፤ ያንጊዜም ኡሳታዊው ሴቦቃይ ከኀያላን ወገን የነበረውን ሲፋይን ገድሎ ጣለው።
ኢያሱ 16:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ምዕራብም እስከ የፍሌጣውያን ዳርቻ እስከ ታችኛው ቤቶሮን ዳርቻ ድረስ ይወርዳል፤ መውጫውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም በምዕራብ በኩል ቍልቍል ወደ የፍሌጣውያን ግዛት እስከ ታችኛው ቤትሖሮን ምድር ይወርድና ወደ ጌዝር ዘልቆ ባሕሩ ላይ ይቆማል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ምዕራብም እስከ የፍሌጣውያን ድንበር እስከ ታችኛው ቤትሖሮን ድንበር እስከ ጌዝር ድረስ ወረደ፥ መጨረሻውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በምዕራብ በኩል ወደሚገኙት ወደ ያፍሌጣውያን ይዞታ በመዝለቅ እስከ ታችኛው ቤትሖሮን ይደርሳል፤ ከዚያም ወደ ጌዜር ያልፍና መጨረሻው የሜድትራኒያን ባሕር ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ምዕራብም እስከ የፍሌጣውያን ዳርቻ እስከ ታችኛው ቤትሖሮን ዳርቻ እስከ ጌዝር ድረስ ወረደ፥ መውጫውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። |
ከዚህም በኋላ በጋዜር ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት እንደ ገና ሆነ፤ ያንጊዜም ኡሳታዊው ሴቦቃይ ከኀያላን ወገን የነበረውን ሲፋይን ገድሎ ጣለው።
ግዛታቸውና ማደሪያቸው ቤቴልና መንደሮችዋ፥ በምሥራቅም በኩል ነዓራን፥ በምዕራብም በኩል ጌዝርና መንደሮችዋ፥ ደግሞም ሴኬምና መንደሮችዋ፥ እስከ ጋዛና እስከ መንደሮችዋ ድረስ፤
ደግሞም ቅጥርና መዝጊያ፥ መወርወሪያም የነበራቸውን የተመሸጉትን ከተሞች ላይኛውን ቤትሖርን፥ ታችኛውንም ቤትሖርን ሠራ።
በዚያ ጊዜም የጋዜር ንጉሥ ኤላም ላኪስን ለመርዳት ወጣ፤ ኢያሱም አንድ ስንኳ ሳይቀር በሰይፍ ስለት እርሱንና ሕዝቡን መታ፤ የዳነም፥ ያመለጠም የለም።
ድንበሩም ከዚያ በደቡብ በኩል ቤቴል ወደምትባል ወደ ሎዛ ዐለፈ፤ ድንበሩም በታችኛው ቤቶሮን ደቡብ በኩል ባለው ተራራ ወደ ማአጣሮቶሬክ ወረደ።
ሁለተኛው ክፍል ወደ ቤቶሮን መንገድ ዞረ፤ ሦስተኛውም ክፍል በገባዖን መንገድ ባለው ወደ ሴቤሮም ሸለቆ በሚመለከተው በዳርቻው መንገድ ዞረ።