La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 16:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የዮ​ሴ​ፍም ልጆች ድን​በ​ራ​ቸው በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በም​ሥ​ራቅ በኩል ካለው ከዮ​ር​ዳ​ኖስ አን​ሥቶ በም​ድረ በዳ​ውና በተ​ራ​ራ​ማው በኩል ከኢ​ያ​ሪኮ ሎዛ ትባል ወደ ነበ​ረ​ችው ቤቴል ይደ​ር​ሳል፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለዮሴፍ ዝርያዎች የተመደበው ድርሻ፣ ከዮርዳኖስ ኢያሪኮ፣ ማለት ከኢያሪኮ ምንጮች በስተምሥራቅ ይነሣና፣ ምድረ በዳውን በማቋረጥ በኰረብታማው አገር አድርጎ ወደ ቤቴል ይወጣል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የዮሴፍም ልጆች ዕጣ በኢያሪኮ ወንዝ አጠገብ በምሥራቁ በኩል ካለው ከዮርዳኖስ አንሥቶ በምድረ በዳው አድርጎ ከኢያሪኮ በተራራማው አገር በኩል ወደ ቤቴል ወጣ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለዮሴፍ ዘሮች የተመደበው የምድሪቱ ደቡባዊ ክፍል በኢያሪኮ አጠገብ ከዮርዳኖስ ወንዝ ይጀምራል፤ ይኸውም ከኢያሪኮ ምንጮች ምሥራቃዊ ጫፍ በመነሣት ወደ በረሓው ይዘልቃል፤ ከኢያሪኮም ተነሥቶ ወደ ኮረብታማው አገር በመውጣት እስከ ቤትኤል ይደርሳል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የዮሴፍም ልጆች ዕጣ በኢያሪኮ አጠገብ በምሥራቁ በኩል ካለው ከዮርዳኖስ አንሥቶ በምድረ በዳውና በተራራማው በኩል ከኢያሪኮ ወደ ቤቴል ወጣ፥

Ver Capítulo



ኢያሱ 16:1
10 Referencias Cruzadas  

የራ​ሔል ልጆች፤ ዮሴፍ፥ ብን​ያም፤


ከም​ና​ሴም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለኤ​ፍ​ሬም አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።


ባዳ​ር​ጊስ፥ ተራ​ብ​ዐ​ምም፥ ኤኖን፤ ሴኬ​ዎ​ዛን፥


በሰ​ሜን በኩል ድን​በ​ራ​ቸው ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ጀመረ፤ ድን​በ​ሩም ከኢ​ያ​ሪኮ አዜብ ወደ ሰሜን ወገን ወጣ፥ ከዚ​ያም በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ወደ ባሕር ወጣ፤ መው​ጫ​ውም የቤ​ቶን ምድ​ብ​ራ​ይ​ጣስ ነበረ።


በሰ​ባ​ትም ክፍል ይከ​ፍ​ሉ​ታል፤ ይሁዳ በደ​ቡብ በኩል በዳ​ር​ቻው ውስጥ ይቀ​መ​ጣል፤ የዮ​ሴ​ፍም ልጆች በሰ​ሜን በኩል በዳ​ር​ቻው ውስጥ ይቀ​መ​ጣሉ።


በደ​ረ​ሱ​ባ​ቸ​ውም ጊዜ ኢያ​ሱና እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከፊ​ታ​ቸው አፈ​ገ​ፈጉ፤ በም​ድረ በዳው መን​ገ​ድም ሸሹ።


የዮ​ሴ​ፍም ልጆች ደግሞ ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበረ።


እነ​ር​ሱም ሰፍ​ረው ቤቴ​ልን ሰለ​ሉ​አት። አስ​ቀ​ድ​ሞም የዚ​ያች ከተማ ስም ሎዛ ይባል ነበር።


በቤ​ት​ሶር ለነ​በሩ፥ በራማ አዜ​ብም ለነ​በሩ፥ በጌ​ትም ለነ​በሩ፥