ኢያሱ 14:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም በዚያ ቀን፦ ‘አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽመህ ተከትለሃልና እግርህ የረገጠው ምድር ለአንተና ለልጆችህ ለዘለዓለም በርግጥ ርስት ይሆናል’ ብሎ ማለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ሙሴ በዚያች ዕለት፣ ‘አምላኬን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ ተከትለኸዋልና እግርህ የረገጣት ምድር ለዘላለም የአንተና የዘርህ ርስት ትሆናለች’ ብሎ ማለልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም በዚያ ቀን እንዲህ ብሎ ማለ፦ ‘አምላኬን ጌታን ፈጽመህ ተከትለሃልና እግርህ የረገጠው ምድር ለአንተና ለልጆችህ ለዘለዓለም በእርግጥ ርስት ይሆናል።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ፦ ‘አምላኬን እግዚአብሔርን በሙሉ ልብህ ስለ ተከተልከው የረገጥከው ምድር ለአንተና ለልጆችህ የዘለዓለም ርስት ይሆናል’ ” ብሎ በዚያን ቀን በመሐላ ቃል ገብቶልኝ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም በዚያ ቀን፦ አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽመህ ተከትለሃልና እግርህ የረገጠው ምድር ለአንተና ለልጆችህ ለዘላለም በእርግጥ ርስት ይሆናል ብሎ ማለ። |
ወደ ምድረ በዳም ወጡ፤ ወደ ኬብሮንም ደረሱ፤ በዚያም የዔናቅ ዘሮች አኪማን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብሮንም በግብፅ ካለችው ከጣኔዎስ ከተማ በፊት ሰባት ዓመታት ተሠርታ ነበር።
ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ በስተቀር፥ እርሱ ግን ያያታል፤ እግዚአብሔርን ፈጽሞ ተከትሎአልና የረገጣትን ምድር ለእርሱ፥ ለልጆቹም እሰጣለሁ።
የእግራችሁ ጫማ የምትረግጣት ስፍራ ሁሉ ለእናንተ ትሆናለች፤ ከምድረ በዳም፥ ከአንጢሊባኖስም፥ ከታላቁም ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ባሕር ድረስ ዳርቻችሁ ይሆናል።
አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለሙሴ ይህን ቃል ከተናገረ በኋላ፥ እስራኤል በምድረ በዳ ሲዞሩ፥ እርሱ እንደ ተናገረኝ እግዚአብሔር እነዚህን አርባ አምስት ዓመታት በሕይወት አኖረኝ፤ አሁንም፥ እነሆ፥ ለእኔ ዛሬ ሰማንያ አምስት ዓመት ሆነኝ።
ሙሴም እንደ ተናገረ ለካሌብ ኬብሮንን ሰጡት፤ ከዚያም ሠላሳ ከተሞችን ወረሰ፤ ከዚያም ሦስቱን የዔናቅ ልጆች አስወገዳቸው።