ዮናስ 4:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ዮናስን፥ “ፈጽመህ ታዝናለህን?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ግን፣ “በውኑ ልትቈጣ ይገባሃልን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም፦ “አንተ ልትቆጣ ተገቢ ነውን?” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም “ይህን ያኽል ልትቈጣ ይገባሃልን?” አለው። |
ዮናስም ከከተማዪቱ ወጣ፤ በከተማዪቱም ፊት ለፊት ተቀመጠ፤ በከተማዪቱም የሚሆነውን እስኪያይ ድረስ በዚያ ለራሱ ዳስ ሠርቶ ከጥላው በታች ተቀመጠ።
እግዚአብሔርም ዮናስን፥ “በውኑ ስለዚች ቅል ታዝናለህን?” አለው። እርሱም፥ “እስክሞት ድረስ እጅግ አዝኛለሁ” አለ።