ዮናስ 1:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉም አንድ ሆነው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ “አቤቱ! አንተ እንደ ወደድህ አድርገሃልና ስለዚህ ሰው ነፍስ አታጥፋን፤ ንጹሕ ደምንም አታድርግብን።” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህ በዚህ ሰው ነፍስ ምክንያት አታጥፋን፤ የዚህ ንጹሕ ሰው ደምም በእኛ ላይ አይሁን፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ የወደድኸውን አድርገሃልና” ብለው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ወደ ጌታ ጮኹ፥ እንዲህም አሉ፦ “ጌታ ሆይ! እባክህ ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ እንለምንሃለን፥ ንጹሕንም ደም በእኛ ላይ አታድርግ፤ ጌታ ሆይ ደስ የሚያሰኝህን አድርገሃልና።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! የዚህ ሰው ሕይወት እንዲጠፋ ብናደርግ አታጥፋን፤ አንተ የፈቀድከውን ስላደረግህ ንጹሕ ደም እንዳፈሰስን አድርገህ አትቊጠርብን!” በማለት ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። |
መርከበኞቹም ፈሩ፤ እያንዳንዱም ወደ አምላኩ ጮኸ፤ መርከቢቱም እንድትቀልልላቸው በውስጥዋ የነበረውን ዕቃ ወደ ባሕር ጣሉት፤ ዮናስ ግን ወደ መርከቡ ውስጠኛው ክፍል ወርዶ ነበር፥ ተኝቶም ያንኳርፍ ነበር።
ሰዎችና እንስሶችም ማቅ ይልበሱ፤ ወደ እግዚአብሔርም በአንድነት ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ከአለው ግፍ ይመለሱ።
አረማውያንም እፉኝቱ በጳውሎስ እጅ ላይ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው፥ “ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ይመስላል፤ ከባሕር እንኳ በደኅና ቢወጣም በሕይወት ይኖር ዘንድ የእግዚአብሔር ፍርድ አልተወውም” አሉ።
አቤቱ፥ ከግብፅ ምድር የተቤዠኸውን ሕዝብህን እስራኤልን ይቅር በል፤ በሕዝብህም በእስራኤል ላይ የንጹሑን ደም በደል አትቍጠር’ ብለው ይናገሩ፤ ስለ ደሙም ይሰረይላቸዋል።