መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፤ ምስፍናም ከአብራኩ፥ ለእርሱ የሚጠብቀውን እስኪያገኝ ድረስ፤ የአሕዛብ ተስፋቸው እርሱ ነውና፤
ዮሐንስ 6:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡም ጌታችን ኢየሱስ ያደረገውን ተአምራት አይተው፥ “ይህ በእውነት ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎቹም ኢየሱስ ያደረገውን ታምራዊ ምልክት ካዩ በኋላ፣ “ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ በርግጥ ይህ ነው” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ የተነሣ ሰዎቹ ኢየሱስ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ “ይህ በእውነት ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው፤” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎቹም ኢየሱስ ያደረገውን ተአምር ባዩ ጊዜ፥ “በእርግጥ ይህ ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው!” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህ የተነሣ ሰዎቹ ኢየሱስ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ፦ ይህ በእውነት ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው አሉ። |
መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፤ ምስፍናም ከአብራኩ፥ ለእርሱ የሚጠብቀውን እስኪያገኝ ድረስ፤ የአሕዛብ ተስፋቸው እርሱ ነውና፤
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ይህ ምንድነው?” አላቸው፤ እነርሱም እንዲህ አሉት፥ “በእግዚአብሔር ፊትና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በቃሉና በሥራው ብርቱ ነቢይና እውነተኛ ሰው ስለነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ፥
ሁሉም ፈሩ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ፤ እንዲህም አሉ፥ “ታላቅ ነቢይ ተነሣልን፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ጐብኝቶአልና።”
“እንኪያ አንተ ማነህ? አንተ ኤልያስ ነህን?” ብለው ጠየቁት፤ “አይደለሁም” አለ፤ “እንኪያ አንተ ነቢዩ ነህን?” አሉት፤ “አይደለሁም” አለ።
እርስዋም፥ “አዎን፥ ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ እንደ ሆንህ እኔ አምናለሁ” አለችው።
ጌታችን ኢየሱስም በቃና ዘገሊላ ያደረገው የተአምራት መጀመሪያ ይህ ነው፤ ክብሩንም ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም አመኑበት።
ሴቲቱንም፥ “እኛ ራሳችን ይህ በእውነት የዓለም መድኀኒት ክርስቶስ እንደ ሆነ ሰምተንና ተረድተን ነው እንጂ በአንቺ ቃል ያመንበት አይደለም” አሏት።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ የምትፈልጉኝ እንጀራ ስለ በላችሁና ስለ ጠገባችሁ ነው እንጂ ተአምራት ስለ አያችሁ አይደለም።
ለእስራኤልም ልጆች፦ ‘እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋልና እርሱን ስሙት’ ያላቸው ይህ ሙሴ ነው።