Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 6:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በበ​ሽ​ተ​ኞ​ችም ላይ ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ራት ስለ አዩ ብዙ ሰዎች ተከ​ተ​ሉት፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ብዙ ሰዎችም በሽተኞችን በመፈወስ ያደረጋቸውን ታምራዊ ምልክቶች ስላዩ ተከተሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በበሽተኞችም ያደረገውን ምልክቶች ስላዩ ብዙ ሕዝብ ተከተለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ብዙ ሰዎች ኢየሱስ በሽተኞችን በመፈወስ ያደረገውን ተአምር ስላዩ ተከተሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በበሽተኞችም ያደረገውን ምልክቶች ስላዩ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 6:2
19 Referencias Cruzadas  

ኢየሱስም አውቆ ከዚያ ፈቀቅ አለ። ብዙ ሰዎችም ተከተሉት፤ ሁሉንም ፈወሳቸው፤ እንዳይገልጡትም አዘዛቸው፤


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቃና ዘገ​ሊላ ያደ​ረ​ገው የተ​አ​ም​ራት መጀ​መ​ሪያ ይህ ነው፤ ክብ​ሩ​ንም ገለጠ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አመ​ኑ​በት።


ሰዎችም ሲሄዱ አዩአቸው፤ ብዙዎችም አወቁአቸውና ከከተሞች ሁሉ በእግር እየሮጡ ወዲያ ቀደሙአቸው፤ ወደ እርሱም ተሰበሰቡ።


ወጥቶም ብዙ ሕዝብ አየና አዘነላቸው፤ ድውዮቻቸውንም ፈወሰ።


ከተራራም በወረደ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት።


እርሱም በታንኳ ገብቶ እስኪቀመጥ ድረስ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ሕዝቡም ሁሉ በወደቡ ቆመው ነበር።


እርሱ ግን ሲወጣ ብዙ ሊሰብክና ነገሩን ሊያወራ ጀመረ፤ ስለዚህም ኢየሱስ ተገልጦ ወደ ከተማ መግባት ወደ ፊት ተሳነው፤ ነገር ግን በውጭ በምድረ በዳ ይኖር ነበር፤ ከየስፍራውም ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በፋ​ሲካ በዓል በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሳለ ብዙ ሰዎች ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ራት ባዩ ጊዜ በስሙ አመኑ።


እር​ሱም በሌ​ሊት ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መጥቶ እን​ዲህ አለው፥ “መም​ህር ሆይ፥ ልታ​ስ​ተ​ምር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እንደ መጣህ እና​ው​ቃ​ለን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ይህን ተአ​ምር ሊያ​ደ​ርግ የሚ​ችል የለ​ምና።”


ሕዝ​ቡም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ራት አይ​ተው፥ “ይህ በእ​ው​ነት ወደ ዓለም የሚ​መ​ጣው ነቢይ ነው” አሉ።


በማ​ግ​ሥ​ቱም ከባ​ሕሩ ዳር ቆመው የነ​በሩ ሰዎች ከአ​ን​ዲት ታንኳ በቀር ከዚያ ሌላ ታንኳ እን​ዳ​ል​ነ​በረ፥ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ለብ​ቻ​ቸው ሄዱ እንጂ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ወደ ታንኳ እን​ዳ​ል​ወጣ አዩ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ንተ የም​ት​ፈ​ል​ጉኝ እን​ጀራ ስለ በላ​ች​ሁና ስለ ጠገ​ባ​ችሁ ነው እንጂ ተአ​ም​ራት ስለ አያ​ችሁ አይ​ደ​ለም።


እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉት፥ “የም​ት​ሠ​ራ​ውን አይ​ተን በአ​ንተ እና​ምን ዘንድ ምን ተአ​ም​ራት ታደ​ር​ጋ​ለህ?


የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ጉባ​ኤ​ውን ሰብ​ስ​በው እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “እነሆ፥ ይህ ሰው ብዙ ተአ​ም​ራት ያደ​ር​ጋል፤ ምን እና​ድ​ርግ?


ስለ​ዚ​ህም ነገር ሕዝቡ ሁሉ ሊቀ​በ​ሉት ወጡ፤ ይህን ተአ​ም​ራት እንደ አደ​ረገ ሰም​ተ​ዋ​ልና።


ይህ​ንም ያህል ተአ​ም​ራት በፊ​ታ​ቸው ሲያ​ደ​ርግ አላ​መ​ኑ​በ​ትም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በዚህ መጽ​ሐፍ ያል​ተ​ጻፈ ብዙ ሌላ ተአ​ም​ራት በደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ፊት አደ​ረገ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios