ዮሐንስ 5:46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴንስ አምናችሁት ቢሆን እኔንም ባመናችሁኝ ነበር፤ እርሱ ስለ እኔ ጽፎአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴን ብታምኑ ኖሮ፣ እኔን ባመናችሁ ነበር፤ ምክንያቱም እርሱ የጻፈው ስለ እኔ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴንስ ብታምኑት እኔንም ባመናችሁ ነበር፤ እርሱ ስለ እኔ ጽፎአልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴን ብታምኑ ኖሮ እርሱ ስለ እኔ ጽፎአልና እኔንም ባመናችሁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴንስ ብታምኑት እኔን ባመናችሁ ነበር፤ እርሱ ስለ እኔ ጽፎአልና። |
ዘርህም እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናል፤ እስከ ባሕርና እስከ አዜብ እስከ መስዕና እስከ ምሥራቅ ይበዛል፤ ይሞላልም፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በአንተ፥ በዘርህም ይባረካሉ።
በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም ሰኰናውን ትነድፋለህ።”
መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፤ ምስፍናም ከአብራኩ፥ ለእርሱ የሚጠብቀውን እስኪያገኝ ድረስ፤ የአሕዛብ ተስፋቸው እርሱ ነውና፤
እግዚአብሔርም አዳነኝና ለታላቁም፥ ለታናሹም እየመሰከርሁ እስከ ዛሬ ደረስሁ፤ ይደረግ ዘንድ ካለው፥ ነቢያት ከተናገሩት፥ ሙሴም ከተናገረው ሌላ ያስተማርሁት የለም።
በኦሪት ሕግ ያሉ ሁሉ በእርግማን ውስጥ ይኖራሉ፤ መጽሐፍ እንዲህ ብሎአልና፥ “በዚህ በኦሪት መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን ሁሉ የማይፈጽምና የማይጠብቅ ርጉም ይሁን።”
እኛንስ ክርስቶስ ስለ እኛ የኦሪትን መርገም በመሸከሙ ከኦሪት መርገም ዋጅቶናል፤ መጽሐፍ እንዲህ ብሎአልና፥ “በእንጨት ላይ የተሰቀለ ሁሉ ርጉም ነው።”