ዮሐንስ 4:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው በወይን ቦታ አቅራቢያ ወደ አለችው ሲካር ወደምትባለው የሰማርያ ከተማ ደረሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በሰማርያ፣ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ቦታ አጠገብ ወደ ነበረች፣ ሲካር ወደምትባል ከተማ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ስፍራ አጠገብ ወደምትገኝ ሲካር ወደምትባል የሰማርያ ከተማ መጣ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ቦታ አጠገብ ወደምትገኝ፥ ሲካር ተብላ ወደምትጠራ የሰማርያ ከተማ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ስፍራ አጠገብ ወደምትሆን ሲካር ወደምትባል የሰማርያ ከተማ መጣ፤ |
እኔም ከአሞራውያን እጅ በሰይፌና በቀስቴ የወሰድሁትን ምርኮ ለአንተ ከወንድሞችህ የተሻለውን እሰጥሃለሁ” አለው።
በቤቴል ባለው መሠዊያ ላይ፥ በሰማርያም ከተሞች ውስጥ ባሉት በኮረብታዎቹ መስገጃዎች ላይ በእግዚአብሔር ቃል የተናገረው ነገር በእውነት ይደርሳልና።”
ይህን ጕድጓድ ከሰጠን ከአባታችን ከያዕቆብ አንተ ትበልጣለህን? እርሱም ልጆቹም፥ ከብቶቹም ከእርሱ ጠጥተዋል።”
በዚያም የያዕቆብ የውኃ ጕድጓድ ነበረ። ጌታችን ኢየሱስም መንገድ በመሄድ ደክሞ በዚያ ጕድጓድ አጠገብ ተቀመጠ፤ ጊዜውም ስድስት ሰዓት ያህል ነበር።
የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ያወጡትን የዮሴፍን አፅም ያዕቆብ በሰቂማ ከሚኖሩ ከአሞራውያን በመቶ በጎች በገዛው ለዮሴፍ ድርሻ አድርጎ በሰጠው እርሻ በአንዱ ክፍል በሰቂማ ቀበሩት።