Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሉቃስ 9:52 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

52 በፊ​ቱም መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ ሄደ​ውም ያዘ​ጋ​ጁ​ለት ዘንድ ወደ ሰማ​ርያ ከተማ ገቡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

52 አስቀድሞም መልእክተኞችን ወደዚያ ላከ። እነርሱም ሁኔታዎችን አስቀድመው ሊያመቻቹለት ወደ አንድ የሳምራውያን መንደር ገቡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

52 እርሱም አስቀድሞ መልክተኞችን ላከ። ሄደውም ሊያሰናዱለት ወደ አንዲት የሳምራውያን መንደር ገቡ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

52 ከእርሱ በፊት ቀድመው የሚሄዱትንም መልእክተኞች ላከ፤ እነርሱም ሁሉን ነገር ለማዘጋጀት በሰማርያ ወደምትገኘው ወደ አንዲት መንደር ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

52 በፊቱም መልክተኞችን ሰደደ። ሄደውም ሊያሰናዱለት ወደ አንድ ወደ ሳምራውያን መንደር ገቡ፤

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 9:52
13 Referencias Cruzadas  

እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፣ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፣ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


እነዚህን ዐሥራ ሁለቱን ኢየሱስ ላካቸው፤ አዘዛቸውም፤ እንዲህም አለ “በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ፤ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ፤


ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ሌሎች ሰባ ሰዎ​ችን መረጠ፤ ሁለት ሁለት አድ​ር​ጎም ሊሄ​ድ​በት ወደ አለው ከተ​ማና መን​ደር በፊቱ ላካ​ቸው።


አንድ ሳም​ራዊ ግን በዚ​ያች መን​ገድ ሲሄድ አገ​ኘው፤ አይ​ቶም አዘ​ነ​ለት።


ከዚህ በኋላ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሲሄድ በሰ​ማ​ር​ያና በገ​ሊላ መካ​ከል ዐለፈ።


በግ​ን​ባ​ሩም ወድቆ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እግር በታች ሰገ​ደና አመ​ሰ​ገ​ነው፤ ሰው​የ​ውም ሳም​ራዊ ነበር።


እነሆ፥ መን​ገ​ድ​ህን በፊ​ትህ የሚ​ጠ​ርግ መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ዬን በፊ​ትህ እል​ካ​ለሁ፥ ተብሎ ስለ እርሱ የተ​ጻ​ፈ​ለት ይህ ነው።


በሰ​ማ​ርያ በኩ​ልም ሲያ​ልፍ ሳለ፥


ያዕ​ቆብ ለልጁ ለዮ​ሴፍ በሰ​ጠው በወ​ይን ቦታ አቅ​ራ​ቢያ ወደ አለ​ችው ሲካር ወደ​ም​ት​ባ​ለው የሰ​ማ​ርያ ከተማ ደረሰ።


ያቺ የሰ​ማ​ርያ ሴትም፥ “አንተ አይ​ሁ​ዳዊ ስት​ሆን፥ እኔም ሳም​ራ​ዊት ስሆን እን​ዴት ከእኔ ዘንድ ውኃ ልት​ጠጣ ትለ​ም​ና​ለህ?” አለ​ችው፤ አይ​ሁድ ከሳ​ም​ራ​ው​ያን ጋር በሥ​ር​ዐት አይ​ተ​ባ​በ​ሩም ነበ​ርና።


አይ​ሁ​ድም፥ “አንተ ሳም​ራዊ እንደ ሆንህ፥ ጋኔ​ንም እንደ አለ​ብህ መና​ገ​ራ​ችን በሚ​ገባ አይ​ደ​ለ​ምን?” ብለው ጠየ​ቁት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos