ዮሐንስ 1:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕይወት በእርሱ ነበረ፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕይወት በርሱ ነበረች፤ ይህች ሕይወት የሰው ብርሃን ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርሱ ሕይወት ነበረች፤ ሕይወትም የሰዎች ብርሃን ነበረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእርሱ ሕይወት ነበረ፤ ይህም ሕይወት የሰዎች ብርሃን ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች። |
ዕውሮችንም በማያውቋት መንገድ አመጣቸዋለሁ፤ የማያውቋትንም ጎዳና እንዲረግጡ አደርጋቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፤ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህንም አደርግላቸዋለሁ፤ አልተዋቸውምም።
ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፣ እናንተም ትወጣላችሁ፥ እንደ ሰባም እምቦሳ ትፈነጫላችሁ።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “ ገና ለጥቂት ጊዜ ብርሃን ከእናንተ ጋር ነው፤ በጨለማ የሚመላለስ የሚሄድበትን አያውቅምና ጨለማ እንዳያገኛችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “የእውነትና የሕይወት መንገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
አብ ሙታንን እንደሚያስነሣቸው፥ ሕይወትንም እንደሚሰጣቸው እንዲሁ ወልድም ለሚወድዳቸው ሕይወትን ይሰጣል።
ዳግመኛም ጌታችን ኢየሱስ፥ “የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃንን ያገኛል እንጂ በጨለማ ውስጥ አይመላለስም” ብሎ ተናገራቸው።
ክርስቶስ እንደሚሞት፥ ከሙታን ተለይቶም አስቀድሞ እንደሚነሣ፥ ለሕዝብና ለአሕዛብ ሁሉ፥ ለመላውም ዓለም እንደሚያበራ።”
መጽሐፍ እንዲሁ ብሎአልና የመጀመሪያው ሰው አዳም በነፍስ ሕያው ሆኖ ተፈጠረ፤ ሁለተኛው አዳም ግን ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው።
“እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፤ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”