ኢዩኤል 2:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድሪቱም ከፊታቸው ትደነግጣለች፤ ሰማይም ይንቀጠቀጣል፤ ፀሐይና ጨረቃም ይጨልማሉ፤ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ይሰውራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድር በፊታቸው ትንቀጠቀጣለች፤ ሰማይም ይናወጣል፤ ፀሓይና ጨረቃ ይጨልማሉ፤ ከዋክብትም ከእንግዲህ ወዲያ አያበሩም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድሪቱም ከፊታቸው ትናወጣለች፥ ሰማያትም ይንቀጠቀጣሉ፥ ፀሐይና ጨረቃም ይጨልማሉ፥ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ይሰውራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በፊታቸው ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ ሰማይም ይናወጣል፤ ፀሐይና ጨረቃም ይጨልማሉ፤ ከዋክብትም ብርሃን የማይሰጡ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድሪቱም ከፊታቸው ትናወጣለች፥ ሰማያትም ይንቀጠቀጣሉ፥ ፀሐይና ጨረቃም ይጨልማሉ፥ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ይሰውራሉ። |
የእግዚአብሔር ሕግ ንጹሕ ነው፤ ነፍስንም ይመልሳል፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትንም ጠቢባን ያደርጋል።
የሰማይም ከዋክብትና ኦሪዎን፥ የሰማይ ሠራዊትም ሁሉ ብርሃናቸውን አይሰጡም፤ ፀሐይም በወጣች ጊዜ ትጨልማለች፤ ጨረቃም በብርሃኑ አያበራም።
የጨለማና የነፋስ ቀን፥ የደመናና የጉም ቀን ነው፤ ታላቅና ብርቱ ሕዝብ በተራሮች ላይ እንደ ወገግታ ተዘርግቶአል፤ ከዘለዓለምም ጀምሮ እንደ እርሱ ያለ አልነበረም፤ ከእርሱም በኋላ እስከ ልጅ ልጅ ድረስ እንደ እርሱ ያለ አይሆንም።
“ጢሮስና ሲዶና የፍልስጥኤም አውራጃ ገሊላም ሁሉ ሆይ! ከእናንተ ጋራ ምን አለኝ? እናንተ በቀልን ትበቀሉኛላችሁን? ቂምንስ ትቀየሙኛላችሁን? ፈጥኜ በችኰላ ፍዳን በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ።
ሁሉን የሚሠራና የሚያቅናና፥ ብርሃኑን ወደ መስዕ የሚመልሰው፥ ቀኑን እንደ ሌሊት የሚያጨልመው፥ የባሕሩንም ውኃ ጠርቶ በምድር ፊት የሚያፈስሰው ስሙ ሁሉን የሚችል ጌታ እግዚአብሔር ነው።
ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፤ ታላቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጕር ጥቁር ሆነ፤ ጨረቃም በሞላው እንደ ደም ሆነ፤
አራተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ የፀሐይ ሲሶና የጨረቃ ሲሶ የከዋክብትም ሲሶ ተመታ፤ የእነዚህ ሲሶ ይጨልም ዘንድ፥ የቀንም ሲሶው እንዳያበራ፥ እንዲሁም የሌሊት።