ኢዮብ 4:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እፍ ብሎባቸዋልና ይደርቃሉ፥ ጥበብም የላቸውምና ይጠፋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያለ ጥበብ ይሞቱ ዘንድ፣ የድንኳናቸው ገመድ አልተነቀለምን?’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገመዳቸው የተነቀለ አይደለምን? አለጥበብም ይሞታሉ።’” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካስማው እንደ ተነቀለ ድንኳን ያለ ጥበብ ይሞታሉ።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገመዳቸው የተነቀለ አይደለምን? አለጥበብም ይሞታሉ። |
አቤቱ አምላኬ፥ ብዙ ተአምራትህን አደረግህ፥ አሳብህንም ምንም የሚመስለው የለም፤ አወራሁ፥ ተናገርሁ፥ ከቍጥርም በዛ።
እግዚአብሔርም፦ አንተ ሰነፍ! በዚች ሌሊት ነፍስህን ከሥጋህ ለይተው ይወስዷታል፤ እንግዲህ ያጠራቀምኸው ለማን ይሆናል? አለው።
ፀሐይ ከትኵሳት ጋር ይወጣልና፥ ሣርንም ያጠወልጋልና፥ አበባውም ይረግፋልና፥ የመልኩም ውበት ይጠፋልና፤ እንዲሁ ደግሞ ባለ ጠጋው በመንገዱ ይዝላል።