እነሆ፥ በምድረ በዳ እንዳሉ እንደ ሜዳ አህዮች ሆኑ። ስለ እኔም ሥራቸውን ትተው ይወጣሉ፤ መብል፦ ከልጅነታቸው ጀምሮ ይጥማቸዋል።
ኢዮብ 39:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በረሃውን ለእርሱ ቤት፥ መኖሪያውንም በጨው ምድር አድርጌ ሰጠሁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድረ በዳውን መኖሪያው፣ የጨውንም ምድር ማደሪያው አድርጌ ሰጠሁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በረሃውን ለእርሱ ቤት አድርጌ ሰጠሁት፥ መኖሪያውም በጨው ምድር ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በረሓን ለእነርሱ መሰማሪያ አድርጌ ሰጥቼአለሁ፤ ጨው ባለበት ሜዳም እንዲኖሩ አድርጌአቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በረሃውን ለእርሱ ቤት አድርጌ ሰጠሁት፥ መኖሪያውም በጨው ምድር ነው። |
እነሆ፥ በምድረ በዳ እንዳሉ እንደ ሜዳ አህዮች ሆኑ። ስለ እኔም ሥራቸውን ትተው ይወጣሉ፤ መብል፦ ከልጅነታቸው ጀምሮ ይጥማቸዋል።
በምድረ በዳ እንደ አለ ቍጥቋጦ ይሆናል፤ መልካምም በመጣ ጊዜ አያይም፤ ሰውም በማይኖርበት፥ ጨው ባለበት ምድር በምድረ በዳ በደረቅ ስፍራ ይቀመጣል።
በምድረ በዳ ባሉ ውኃዎች ተዘረጋች፤ በሰውነቷም ምኞት ትወሰዳለች፤ ይይዟታል፤ የሚመልሳት ግን የለም፤ የሚሹአትም አይደክሙም፤ በተዋረደችበትም ጊዜ ያገኙአታል።
ለብቻውም እንደሚቀመጥ እንደ ምድረ በዳ አህያ ወደ አሦር ወጥተዋል፤ ኤፍሬምም እንደ ገና ለመለመ፤ እጅ መንሻንም ወደደ።
ምድርም በሁለንተናዋ ዲንና ጨው፥ መቃጠልም እንደ ሆነባት፥ እንዳይዘራባትም፥ እንዳታበቅልም፥ ማናቸውም ሣርና ልምላሜም እንዳይወጣባት፥ እግዚአብሔር በቍጣውና በመዓቱ እንደ ገለበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና እንደ ሲባዮ እንደ ሆነች ባዩ ጊዜ፥