Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 39:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በረሓን ለእነርሱ መሰማሪያ አድርጌ ሰጥቼአለሁ፤ ጨው ባለበት ሜዳም እንዲኖሩ አድርጌአቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ምድረ በዳውን መኖሪያው፣ የጨውንም ምድር ማደሪያው አድርጌ ሰጠሁት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በረሃውን ለእርሱ ቤት አድርጌ ሰጠሁት፥ መኖሪያውም በጨው ምድር ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በረ​ሃ​ውን ለእ​ርሱ ቤት፥ መኖ​ሪ​ያ​ው​ንም በጨው ምድር አድ​ርጌ ሰጠ​ሁት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በረሃውን ለእርሱ ቤት አድርጌ ሰጠሁት፥ መኖሪያውም በጨው ምድር ነው።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 39:6
9 Referencias Cruzadas  

“ድኾች በበረሓ እንዳሉ የሜዳ አህዮች ለልጆቻቸው ምግብ ለመፈለግ ወጥተው ይንከራተታሉ፤


ሁካታ ከበዛባቸው ከተሞች ርቀው ይኖራሉ፤ ከኋላ እየነዳ የሚጮኽባቸውን አይቀበሉም።


እዚያ ከሚኖሩት ሰዎች ክፋት የተነሣ ፍሬያማዋን አገር እንደ ጨው ምድር የማታፈራ አደረጋት።


የሜዳ አህዮች ከውሃ ጥም የተነሣ፥ በየኰረብታው ጫፍ ላይ ቆመው እንደ ቀበሮ ያለከልካሉ፤ ምግብ ስለማያገኙም የማየት ኀይላቸው ይቀንሳል።


እንዲህ ዐይነቱ ሰው ማንም ሊኖርበት በማይችል በጨው ምድርና በበረሓ እንደሚበቅል ቊጥቋጦ ነው፤ በሕይወቱ ሙሉ ምንም መልካም ነገርን አያገኝም።


በበረሓ መኖርን የለመደች የሜዳ አህያ፥ ፍትወት በተቀሰቀሰባት ጊዜ ማን ሊቈጣጠራት ይችላል? ወንዶች የሜዳ አህዮች ያሉበትን ስፍራ፥ ራስዋ አነፍንፋ ስለምትደርስበት፥ እነርሱ እርስዋን በመፈለግ መድከም አያስፈልጋቸውም።


ነገር ግን ረግረጉና እቋሪው ውሃ የጨው መከማቻ እንደ ሆነ ይቀራል እንጂ የጠራ ውሃ አይሆንም።


ብቻውን እንደሚንከራተት የምድረ በዳ አህያ ወደ አሦር ሄዱ፤ እንዲጠብቁአቸውም ዋጋ በመክፈል መንግሥታትን ተለማመጡ፤


ምድሪቱም ሁሉ በዲንና በጨው ትሸፈናለች፤ ምንም ነገር አይተከልባትም፤ ምንም ነገር አታበቅልም፤ እግዚአብሔር በኀይለኛ ቊጣው እንደ ደመሰሳቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና እንደ ጺባዮ ትሆናለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos