Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 24:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እነሆ፥ በም​ድረ በዳ እን​ዳሉ እንደ ሜዳ አህ​ዮች ሆኑ። ስለ እኔም ሥራ​ቸ​ውን ትተው ይወ​ጣሉ፤ መብል፦ ከል​ጅ​ነ​ታ​ቸው ጀምሮ ይጥ​ማ​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በምድረ በዳ እንዳሉ የሜዳ አህዮች፣ ድኾች ምግብ ፍለጋ ይራወጣሉ፤ ከበረሓው ምድር ለልጆቻቸው ምግብ ይሻሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እነሆ፥ በምድረ በዳ እንዳሉ እንደ ሜዳ አህዮች፥ መብልን ፈልገው ወደ ሥራቸው ይወጣሉ፥ ምድረ በዳውም ለልጆቻቸው መብልን ይሰጣቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “ድኾች በበረሓ እንዳሉ የሜዳ አህዮች ለልጆቻቸው ምግብ ለመፈለግ ወጥተው ይንከራተታሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እነሆ፥ በምድር በዳ እንዳሉ እንደ ሜዳ አህዮች፥ መብልን ፈልገው ወደ ሥራቸው ይወጣሉ፥ ምድረ በዳውም ለልጆቻቸው መብልን ይሰጣቸዋል።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 24:5
16 Referencias Cruzadas  

እር​ሱም የበ​ረሃ ሰው ይሆ​ናል፤ እጁ በሁሉ ላይ ይሆ​ናል፤ የሁ​ሉም እጅ ደግሞ በእ​ርሱ ላይ ይሆ​ናል፤ እር​ሱም በወ​ን​ድ​ሞቹ ሁሉ ፊት ይኖ​ራል።”


በሰ​ይ​ፍ​ህም ትኖ​ራ​ለህ፤ ለወ​ን​ድ​ም​ህም ትገ​ዛ​ለህ፤ ነገር ግን ቀን​በ​ሩን ከአ​ን​ገ​ትህ ልት​ጥል ብት​ወ​ድድ ከእ​ርሱ ጋር ተስ​ማማ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​ስ​ቈ​ጡ​ትን ሰዎች፥ እርሱ የሚ​መ​ረ​ም​ራ​ቸው አይ​ደ​ለ​ምን?


ሥራ​ቸ​ው​ንም ዐውቆ ለጨ​ለማ ዳረ​ጋ​ቸው። በሌ​ሊ​ትም እንደ ሌባ ናቸው።


“የራ​ሳ​ቸው ያል​ሆ​ነ​ውን እርሻ ያለ ሰዓቱ ያጭ​ዳሉ። ኃጥ​ኣን ድሆ​ችን በወ​ይ​ና​ቸው ቦታ ያለ ዋጋና ያለ ቀለብ ያሠ​ሩ​አ​ቸ​ዋል።


እነ​ርሱ የሰ​በ​ሰ​ቡ​ት​ንም ጻድ​ቃን ይበ​ሉ​ታል። እነ​ር​ሱን ግን ክፋት ቷጋ​ቸ​ዋ​ለች፥ ኀይ​ላ​ቸ​ውም ይደ​ክ​ማል።


እስ​ራ​ኤ​ልም ወደ ግብፅ ገባ፥ ያዕ​ቆ​ብም በካም ምድር ተቀ​መጠ።


ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፥ ከዐይናቸው እንቅልፋቸው ይወገዳል አይተኙምም።


በም​ድረ በዳ ባሉ ውኃ​ዎች ተዘ​ረ​ጋች፤ በሰ​ው​ነ​ቷም ምኞት ትወ​ሰ​ዳ​ለች፤ ይይ​ዟ​ታል፤ የሚ​መ​ል​ሳት ግን የለም፤ የሚ​ሹ​አ​ትም አይ​ደ​ክ​ሙም፤ በተ​ዋ​ረ​ደ​ች​በ​ትም ጊዜ ያገ​ኙ​አ​ታል።


እያ​ደቡ ልባ​ቸ​ውን እንደ ምድጃ አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ዋል፤ ጋጋ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ሌሊ​ቱን ሁሉ አን​ቀ​ላፋ፤ በጠ​ባም ጊዜ እንደ እሳት ነበ​ል​ባል ይነ​ድ​ዳል።


ለብ​ቻ​ውም እን​ደ​ሚ​ቀ​መጥ እንደ ምድረ በዳ አህያ ወደ አሦር ወጥ​ተ​ዋል፤ ኤፍ​ሬ​ምም እንደ ገና ለመ​ለመ፤ እጅ መን​ሻ​ንም ወደደ።


በመኝታቸው ላይ በደልን ለሚያስቡ ክፋትንም ለሚያደርጉ ወዮላቸው! ኃይል በእጃቸው ነውና ሲነጋ ይፈጽሙታል።


በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ እንደሚያገሡ አንበሶች ናቸው፣ ፈራጆችዋም እስከ ነገ ድረስ ምንም እንደማያስቀሩ እንደ ማታ ተኵላዎች ናቸው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ከቀ​ያፋ ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ ወሰ​ዱት፤ አይ​ሁድ ግን ፈጽሞ ስለ ነጋ የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ ሳይ​በሉ እን​ዳ​ይ​ረ​ክሱ ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ አል​ገ​ቡም።


በነ​ጋም ጊዜ አይ​ሁድ ተሰ​ብ​ስ​በው፥ ጳው​ሎ​ስን እስ​ኪ​ገ​ድ​ሉት ድረስ እን​ዳ​ይ​በ​ሉና እን​ዳ​ይ​ጠጡ ተስ​ማ​ም​ተው ተማ​ማሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos